عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«كان رجلٌ يُدَايِنُ الناسَ، فكان يقول لفتاه: إذا أتيتَ مُعسِرًا فتجاوز عنه، لعل اللهَ يَتجاوزُ عنا، فلقي اللهَ فتجاوز عنه».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1562]
المزيــد ...
ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ረሱል የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡
"ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን የተቸገረ ካጋጠመህ እለፈው።' (ሞተና) አላህንም ተገናኘ፤ አላህም ይቅር አለው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1562]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰዎች ጋር በመበዳደር የሚንቀሳቀስ ወይም በዱቤ የሚሸጥላቸው ስለሆነ ሰው ተናገሩ። ለሰዎች ያበደረውን ብድር ለሚቀበልለት ሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ "ተበዳሪ ዘንድ ስትሄድ እዳውን መክፈል ተስኖት ካገኘሀው እለፈው" ይህም የሚከፍልበትን ፋታ በመስጠት፣ እዳውን በመፈለግ ላይ ችክ ባለማለት ወይም ጥቂት ቢጎድልም ያለውን በመቀበል ሊሆን ይችላል። ይህንንም የሚያደርገው አሏህ የእርሱንም ወንጀል እንዲያልፍለትና ይቅር እንዲለው ከመከጀል አኳያ ነበር። በሞተም ጊዜ አሏህም ማረው፤ ወንጀሉንም ይቅር አለለት።