+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم كان يقول:
«الصَّلَوَاتُ الْخَمْسُ، وَالْجُمُعَةُ إِلَى الْجُمُعَةِ، وَرَمَضَانُ إِلَى رَمَضَانَ، مُكَفِّرَاتٌ مَا بَيْنَهُنَّ إِذَا اجْتَنَبَ الْكَبَائِرَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 233]
المزيــد ...

ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ይሉ ነበር፡
"ከባባዶቹን ወንጀሎች ከተጠነቀቁ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 233]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከባባዶቹን ወንጀሎች መጠንቀቅ እንደቅድመ መስፈርት ከተሟላ አምስቱ በቀንና ሌሊት የሚከናወኑት ሶላቶች፣ በየሳምንቱ የሚሰገደው የጁምዐ ሶላትና በየአመቱ የረመዳንን ወር መፆም በመካከላቸው የሚፈፀምን ትናንሽ ወንጀሎችን እንደሚያስምሩ ነገሩን። ዝሙትና መጠጥን የመሰሉ ከባባድ ወንጀሎች በተውባ ካልሆነ በቀር አይሰረዙም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht Azerisht الأوزبكية الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከወንጀሎች መካከል ከባባድና ትናንሽ የሚባሉ እንዳሉ፤
  2. ትናንሽ ወንጀሎች የሚሰረዙት ከባባዶቹን ወንጀሎች መራቅን እንደመስፈርት ማሟላት ከተቻለ መሆኑን እንረዳለን።
  3. ከባባድ ወንጀሎች የሚባሉት ወይ በዱኒያ ቅጣት የተወሰነባቸው፣ ወይም በአኼራ የሚያስከትሉትን የቅጣት አይነት የተነገረባቸው፣ ወይም የአላህ ቁጣ የመጣባቸው፣ ወይም ከባድ ዛቻ ያለባቸው፣ ወይም ደግሞ አድራጊው የተረገመባቸው ሲሆኑ ነው። ለምሳሌ፡ ዝሙት፣ መጠጥ መጠጣት ይጠቀሳሉ።