عن المقدام بن معدِيْكَرِب رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«أَلَا هَلْ عَسَى رَجُلٌ يَبْلُغُهُ الْحَدِيثُ عَنِّي وَهُوَ مُتَّكِئٌ عَلَى أَرِيكَتِهِ فَيَقُولُ: بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ كِتَابُ اللهِ، فَمَا وَجَدْنَا فِيهِ حَلَالًا اسْتَحْلَلْنَاهُ، وَمَا وَجَدْنَا فِيهِ حَرَامًا حَرَّمْنَاهُ، وَإِنَّ مَا حَرَّمَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَمَا حَرَّمَ اللهُ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه] - [سنن الترمذي: 2664]
المزيــد ...
አልሚቅዳም ቢን መዕዲከሪብ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፡- “የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡-
"አዋጅ! ከእኔ የሆነ ሐዲሥ ወደ አንዱ በአልጋው ላይ እንደተደገፈ ይደርሰውና፡ "በእኛና በእናንተ መካከል (የሚዳኘን) የአላህ መጽሐፍ ነው። በውስጡ የተፈቀደ ሆኖ ያገኘነውን (ብቻ) እንደ ሐላል እንቆጥረዋለን በውስጡም ሐራም ሆኖ ያገኘነውን (ብቻ) እንደ ሐራም እንቆጥረዋለን።" የሚልበት ወቅት ቅርብ ነው። በእርግጥ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሐራም (እርም) ያደረጉት ማንኛውም ነገር አላህ ሐራም እንዳደረገው ነው።'”
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2664]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከሰዎች መካከል የተወሰኑ ሰዎች አንድ ፍራሹ ላይ የተደገፈ ሰው፥ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሐዲሥ ሲደርሰው "በጉዳዮቻችን ላይ በእኛና በናንተ መካከል የሚዳኘን የተከበረው ቁርኣን ነው፤ እሱ በቂያችን ነው፤ በቁርኣን ውስጥ ያገኘነውን ሐላሎች (ፍቁድ) እንሰራበታለን፤ ቁርኣን ውስጥ ያገኘነውን ሐራሞች (እርሞች) እንርቀዋለን። " የሚልበት ዘመን እንደቀረበ ተናገሩ። ቀጥለው ሁሉም በሱናቸው (ሀዲሳቸው) እርም ያደረጉት ወይም የከለከሉት ነገር ደረጃው ልክ አላህ በቁርኣኑ እንደከለከለው አምሳያ እንደሆነ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አብራሩ። ምክንያቱም እሳቸው የጌታቸውን መልዕክት አድራሽ ናቸውና።