عن أبي سعيد الخُدْريِّ رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«مَنْ رَأَى مِنْكُمْ مُنْكَرًا فَلْيُغَيِّرْهُ بِيَدِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِلِسَانِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِقَلْبِهِ، وَذَلِكَ أَضْعَفُ الْإِيمَانِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 49]
المزيــد ...
አቡ ሰዒድ አል'ኹድሪይ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ ፡- የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡-
"ከእናንተ መካከል መጥፎ ሢሠራ የተመለከተ፥በእጁ ይለውጠው (ያስተካክለው)፤ ይህንን ካልቻለ በምላሱ ይከላከል፤ ይህንንም ካልቻለ በቀልቡ (ልቡ) ይጥላ ይህ ግን ደካማው የኢማን ክፍል ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 49]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በቻልነው መጠን መጥፎ ነገርን እንድንለውጥ ( እንድናስወግድ) አዘዋል። መጥፎ ነገር የሚባለውም፥ አላህና መልክተኛው የከለከሏቸው ሁሉም ነገሮች ናቸው። መጥፎ ነገርን ከተመለከተ አቅም ካለው በእጁ የመለወጥ 0(የማስወግድ)ግዴታ አለበት። ይህን ማድረግ ከተሳነው ደግሞ መጥፎ ነገር ፈፃሚውን በመከልከል፣ ጉዳቱን ለሱ በማብራራት፣ ከዚህ እኩይ ተግባር ፈንታ እሱን ወደ መልካም በመምራት በአንደበቱ ይለውጠው። ይህኛዉ የመለወጥ እርከን ከተሳነውም ይህን መጥፎ ነገር በመጥላት፣ ለመለወጥ አቅም ቢኖረው ኖሮ እንደሚለውጠው በመቁረጥ በቀልቡ ይለውጠው። በቀልብ መለወጥ (መጥላት) መጥፎ ነገርን የመለወጥ እጅግ ደካማው የኢማን እርከን ነው።