+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه عن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«مَا نَقَصَتْ صَدَقَةٌ مِنْ مَالٍ، وَمَا زَادَ اللهُ عَبْدًا بِعَفْوٍ إِلَّا عِزًّا، وَمَا تَوَاضَعَ أَحَدٌ لِلهِ إِلَّا رَفَعَهُ اللهُ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2588]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል:-
"ምፅዋት (ከሰጪው) ገንዘብ ላይ አታጎድልም፤ አላህ ለአንድ ባሪያ ይቅር በማለቱ (ምክንያት) ከልቅና በስተቀር አይጨምርለትም፤ አንድም ሰው ለአላህ ብሎ አይተናነስም አላህ ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጂ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2588]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ምፅዋት ከሰጪው ላይ መከራን ትከላከላለች እንጂ ገንዘቡን እንደማታጎድል፤ አላህ ለሰጪው ትልቅ መልካምን እንደሚተካለትና መመፅወቱ ጭማሪ እንጂ ጉድለት እንደማይሆን ገለፁ።
መበቀል ወይም ባለቤቱን መቅጣት እየተቻለም ይቅር ማለት ኃይልና ልቅናን እንጂ አይጨምርም።
አንድም ሰው ማንንም ፈርቶ፣ ለማስመሰልና ከሱ ጥቅም ፈልጎ ሳይሆን ለአላህ ፊት ብሎ አይተናነስምም ዝቅ አይልምም ምንዳው ልቅናና ከፍታ ቢሆን እንጂ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Oromisht Kannadisht Azerisht الأوزبكية الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አንዳንድ ሰዎች ከዚህ ተቃራኒ ቢያስቡም መልካምና ስኬት የሚገኘው ሸሪዐን በመተግበርና መልካምን በመፈፀም ነው።