عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«لَيْسَ الشَّدِيدُ بِالصُّرَعَةِ، إِنَّمَا الشَّدِيدُ الَّذِي يَمْلِكُ نَفْسَهُ عِنْدَ الْغَضَبِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6114]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡
"ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6114]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትክክለኛ ሀይል አካላዊ ሀይል ወይም ጉልበተኞችን የሚጥል ሳይሆን ብርቱና ሀይለኛ የሚባለው ቁጣው በሚበረታ ወቅት ነፍሱን የታገለና ያሸነፋት መሆኑን ገለፁ። ምክንያቱም ይህ ሰው ነፍሱን የመቆጣጠርና ሰይጣንን የማሸነፍ አቅም እንዳለው ይጠቁማልና።