عن أبي ذر رضي الله عنه قال: قال لي النبي صلى الله عليه وسلم:
«لَا تَحْقِرَنَّ مِنَ الْمَعْرُوفِ شَيْئًا، وَلَوْ أَنْ تَلْقَى أَخَاكَ بِوَجْهٍ طَلْقٍ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2626]
المزيــد ...
ከአቡ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉኝ:
"ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2626]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትንሽም ብትሆን እንኳ መልካምን ከመፈፀም እንዳናሳንስ አነሳሱን። ከነዚህ መካከልም ከሙስሊም ጋር በሚገናኝ ወቅት በፈገግታ ፊትን መፍታት ይጠቀሳል። አንድ ሙስሊም ይህን በመፈፀሙ ምክንያት ሙስሊም ወንድሙን ማዝናናትና በውስጡ ደስታን መጨመር ስለሚያመጣ በዚህ ላይ ሊጓጓ ይገባል።