+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«حُجِبَتِ النَّارُ بِالشَّهَوَاتِ، وَحُجِبَتِ الْجَنَّةُ بِالْمَكَارِهِ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6487]
المزيــد ...

ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ረሱል የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡
"ጀሀነም ነፍስያ በምትወዳቸው ስሜታዊ ነገሮች ተጋረደች፤ ጀነት ደግሞ ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተጋረደች።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6487]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጀሀነም ክልክልን በመዳፈርና ግዴታን ባለመወጣት የመሰሉ ነፍስያ በምትፈልጋቸው ነገሮች መሸፈኗን መከበቧን ገለፁ። በመሆኑም የነፍስያውን ፍላጎት በዚህ ረገድ የተከተለ ለጀሀነም ተገባ። ጀነት ደግሞ ትእዛዝ ላይ በመዘውተር፣ ክልከላን በመተውና በዚሁ ላይ ትዕግስት በማድረግ በመሰሉ ነፍስያ በምትጠላቸው ነገሮች መሸፈኗንና መከበቧን አብራሩ። ስለዚህም በዚህ ረገድ በቁርጠኝነት ነፍስያውን የታገለ ለጀነት የተገባ ሆነ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأكانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በስሜት ላይ ለመውደቅ ሰበብ ከሚሆኑ መሰናክሎች መካከል አስቀያሚና የተወገዘ የሆነውን ነገር ነፍስያ ወዳው እስክትዘነበልለት ድረስ ሸይጧን ማስዋቡ አንዱ መሆኑን፤
  2. ወደ ጀሀነም እሳት መዳረሻ ከመሆናቸው አንፃር ከተከለከሉ ፍላጎቶች መራቅና ወደ ጀነት የሚያደርሱ ከመሆናቸው አንፃርም የምንጠላቸው ነገሮች ላይ መታገስን መታዘዛችን ፤
  3. ነፍስያን መታገል፣ በዒባዳ ላይም መትጋት፣ በአምልኮ ዙርያ ያሉ የምንጠላቸውና የሚያስቸግሩን ነገሮች ላይም መታገስ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።