عن ابنِ عُمَرَ رضي الله عنهما قال: قال رسولُ الله صلَّى الله عليه وسلم:
«مَن تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ».
[حسن] - [رواه أبو داود وأحمد] - [سنن أبي داود: 4031]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱው ይመደባል።"
[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4031]
የነርሱ መለዮ የሆነን እምነት ወይም አምልኮ ወይም ተለምዷዊ ነገርን በማድረግ ከከሀዲያን ወይም ከአመፀኞች ወይም ከደጋግ ህዝቦችም ጋር የተመሳሰለ ሰው ከነርሱ እንደሚመደብ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። ምክንያቱም በውጫዊ ማንነት ከነርሱ ጋር መመሳሰል በውስጣዊ ማንነት ከነርሱ ጋር ወደ መመሳሰል ያደርሳልና። ከሆኑ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በነሱ የመደነቅ ውጤት መሆኑ ጥርጥር የሌለው ጉዳይ ነው። ቀስ በቀስም እነሱን ወደመውደድ ፣ ወደማላቅ፣ ወደነርሱ ጥገኛ ወደመሆን ያደርሳል። ይህም አላህ ይጠብቀንና ሰውዬውን በውስጣዊ አመለካከቱና አምልኮው ሳይቀር ከነርሱ ጋር ወደመመሳሰል ይጎትተዋል።