+ -

عن أبي بَكرة رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«إِذَا الْتَقَى الْمُسْلِمَانِ بِسَيْفَيْهِمَا فَالْقَاتِلُ وَالْمَقْتُولُ فِي النَّارِ»، فَقُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ هَذَا الْقَاتِلُ، فَمَا بَالُ الْمَقْتُولِ؟ قَالَ: «إِنَّهُ كَانَ حَرِيصًا عَلَى قَتْلِ صَاحِبِهِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 31]
المزيــد ...

ከአቢ በክረህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦
"ሁለት ሙስሊሞች በሰይፋቸው (ሊጋደሉ) የተገናኙ ጊዜ ገዳዩም ሆነ ተገዳዩ እሳት ውስጥ ናቸው። " እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህ ገዳይ ሆኖ (እሳት መግባቱ መልካም) ተገዳዩ (እሳት የሚገባው) በምን ጥፋቱ ነው?" አልኩ። እርሳቸውም "እሱ ባልደረባውን ለመግደል ጉጉ ስለነበር ነው።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 31]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁለት ሙስሊሞች እርስ በርሳቸው እያንዳንዳቸው የባልደረባውን ህይወት ማጥፋትን ቋምጠው በሰይፋቸው ሊጋደሉ የተገናኙ እንደሆነ ሁለቱም እሳት እንደሚገቡ ተናገሩ። ገዳዩ ባለደረባውን በመግደሉ ምክንያት እሳት ውስጥ ይገባል። ሰሐቦች የተገዳዩ እሳት መግባት ግራ አጋባቸው: እንዴት የእሳት ይሆናል? ብለው ጠየቁ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረባውን ለመግደል በመጓጓቱ ፤ በገዳዩ ከመቀደም በስተቀር ከመግደል ምንም የከለከለው ነገር ስለሌለ እሱም ጭምር የእሳት መሆኑን ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ወንጀል ለመስራት በልቡ የቆረጠና መዳረሻዎቹን የፈፀመ ሰው ለቅጣት የተገባ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ሙስሊሞች እርስ በርስ በመጋደላቸው ዙሪያ ብርቱ ማስጠንቀቂያና የእሳት ዛቻም መምጣቱን እንረዳለን።
  3. በሙስሊሞች መካከል የተፈጠረው መጋደል ትክክል በሆነ ጉዳይ ከሆነ ዛቻ ውስጥ አይካተትም። ለምሳሌ ከመሪ ትእዛዝ የወጡ ወሰን አላፊዎችና ሀገር የሚያበላሹን መዋጋትን ይመስል።
  4. ከባድ ወንጀል የሰራ ሰው በመስራቱ ብቻ ከሀዲ አይሆንም። ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁለቱን እርስ በርስ የሚጋደሉትን ሙስሊሞች ብለው ጠርተዋቸዋልና።
  5. ሁለት ሙስሊሞች በማንኛውም ለመግደል የሚያደርስ በሆነ መሳሪያ ሊጋደሉ ተገናኝተው አንዱ አንዱን ቢገድል ገዳዩም ተገዳዩም እሳት ውስጥ ናቸው። ሐዲሡ ውስጥ ሰይፍ መጠቀሱ ለምሳሌ ያክል ብቻ ነው።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري الفولانية Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأكانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ