+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم:
«اللهُمَّ لَا تَجْعَلْ قَبْرِي وَثَنًا، لَعَنَ اللهُ قَوْمًا اتَّخَذُوا قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ مَسَاجِدَ».

[صحيح] - [رواه أحمد] - [مسند أحمد: 7358]
المزيــد ...

አቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፏል፡
"አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት አታድርግብኝ፤ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው በያዙ ህዝቦች ላይ የአሏህ እርግማን ሰፈነባቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሙስነድ አሕመድ - 7358]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ቀብራቸውን በማላቅና የሱጁድ አቅጣጫውን ወደዛው በማድረግ ሰዎች እንደሚያመልኩት ጣኦት እንዳያደርግባቸው አምላካቸውን ተማፀኑ፤ ከዚያም የነቢያቶችን መቃብር የአምልኮ ስፍራ አድርገው በሚይዙ ላይ የአሏህ እርግማን እንደሰፈነባቸውና ከእዝነቱም እንዳባረራቸው አሳወቁ። ምክንያቱም መቃብሩን የአምልኮ ስፍራ አድርጎ መያዝ የቀብሩን ባለቤት እንዲመለክ ለማድረግና በተቀበረበት አካል ዙርያ አጉል እምነት ለማሳደር መዳረሻ ነውና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأكانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የነብያትና የጻድቃን ሰዎች መቃብርን በተመለከተ ሸሪዓው ያስቀመጠውን ገደብ ማለፉ ከአላህ ሌላ የሚመለኩ ጣኦት እንዲሆኑ ስለሚያደርጋቸው ወደ ሽርክ (ሽርክ) ከሚመሩ መንገዶች መጠንቀቅ እንደሚገባ፤
  2. የተቀበረበት አካል ወደ አሏህ ምንም አይነት ቅርበት ቢኖረውም ቀብሩን ለማላቅም ይሁን በመቃብሩ አሏህን ለማምለክ ማለም እንደማይፈቀድ፤
  3. መስገጃን መቃብር ላይ መገንባት የተከለከለ መሆኑን፤
  4. ሶላተል ጀናዛ ላልተሰገደበት ሰው ሊሰግዱበት ካልሆነ በቀር መስጂድ ባይገነቡም መቃብር ዘንድ መስገድ የተከለከለ መሆኑን እንረዳለን።