+ -

عن جَرِيْر بنِ عبدِ الله رضي الله عنه قال:
كُنَّا عِنْدَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَنَظَرَ إِلَى الْقَمَرِ لَيْلَةً -يَعْنِي الْبَدْرَ- فَقَالَ: «إِنَّكُمْ سَتَرَوْنَ رَبَّكُمْ كَمَا تَرَوْنَ هَذَا الْقَمَرَ، لَا تُضَامُونَ فِي رُؤْيَتِهِ، فَإِنِ اسْتَطَعْتُمْ أَنْ لَا تُغْلَبُوا عَلَى صَلَاةٍ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ غُرُوبِهَا فَافْعَلُوا» ثُمَّ قَرَأَ: «{وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ الْغُرُوبِ}»

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 554]
المزيــد ...

ጀሪር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል:
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ነበርን። የ14ኛዋን ሌሊት ጨረቃ ተመለከቱና እንዲህ አሉ: ' ይህን ጨረቃ እንደምትመለከቱት ጌታችሁንም በርግጥ ታያላችሁ። እርሱን ለማየትም ምንም አትቸገሩም። ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለው ሶላት ላይ አለመሸነፍን ከቻላቹ አድርጉት።' ቀጥሎ ይህንን አንቀፅ አነበቡ: '{ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሀይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው።}'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 554]

ትንታኔ

አንድ ምሽት ላይ ሶሐቦች ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበሩ። የ14ኛዋን ምሽት ጨረቃ ተመለከቱና እንዲህ አሉ: አማኞች ጌታቸውን ያለምንም ጥርጥር በዓይኖቻቸው በእውነት ያዩታል። የበላይ የሆነውን አላህ በሚያዩት ወቅት ምንም አይገፋፉምም፣ ልፋትና ችግርም አያገኛቸውም። ቀጥለውም የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: ከፈጅር ሶላትና ከዐስር ሶላት የሚከለክሏችሁን ምክንያቶች መግታት ከቻላችሁ አድርጉት። ሁለቱንም ሶላቶች በወቅታቸው በህብረት በተሟላ መልኩ ፈፅሙ። ይህ ወደ አላህ ፊት ለመመልከት ከምክንያቶች መካከል አንዱ ነውና። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህቺን አንቀፅ አነበቡ: {ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሀይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው።}

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht Oromisht Kannadisht الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የኢማን ባለቤቶች ጀነት ውስጥ አላህን እንደሚመለከቱት ብስራት እንዳላቸው እንረዳለን።
  2. ከዳዕዋ መንገዶች መካከል: ጉዳይን ማጠንከር፣ ማነሳሳትና ምሳሌን መጥቀስ ጥቂቶቹ ናቸው።