ምድቡ:
+ -

عَنْ أَبِي عَبْدِ الرَّحْمَنِ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ:
حَدَّثَنَا رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَهُوَ الصَّادِقُ المَصْدُوقُ: «إِنَّ أَحَدَكُمْ يُجْمَعُ خَلْقُهُ فِي بَطْنِ أُمِّهِ أَرْبَعِينَ يَوْمًا، ثُمَّ يَكُونُ عَلَقَةً مِثْلَ ذَلِكَ، ثُمَّ يَكُونُ مُضْغَةً مِثْلَ ذَلِكَ، ثُمَّ يُرْسَلُ إلَيْهِ المَلَكُ فَيَنْفُخُ فِيهِ الرُّوحَ، وَيُؤْمَرُ بِأَرْبَعِ كَلِمَاتٍ: بِكَتْبِ رِزْقِهِ، وَأَجَلِهِ، وَعَمَلِهِ، وَشَقِيٍّ أَوْ سَعِيدٍ؛ فَوَالَّذِي لَا إلَهَ غَيْرُهُ إنَّ أَحَدَكُمْ لَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ الجَنَّةِ حَتَّى مَا يَكُونُ بَيْنَهُ وَبَيْنَهَا إلَّا ذِرَاعٌ فَيَسْبِقُ عَلَيْهِ الكِتَابُ فَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ النَّارِ فَيَدْخُلُهَا، وَإِنَّ أَحَدَكُمْ لَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ النَّارِ حَتَّى مَا يَكُونُ بَيْنَهُ وَبَيْنَهَا إلَّا ذِرَاعٌ، فَيَسْبِقُ عَلَيْهِ الكِتَابُ فَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ الجَنَّةِ فَيَدْخُلُهَا».

[صحيح] - [رواه البخاري ومسلم] - [الأربعون النووية: 4]
المزيــد ...

ከአቡ ዐብዱራሕማን ዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
«እውነተኛና እውነት የሚባሉት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ይህንን) ነገሩን፦ "የአንዳችሁ ፍጥረት በእናቱ ሆድ ውስጥ ለአርባ ቀን ይሰበሰባል። ከዚያም በተመሳሳይ የቀናት ብዛት የረጋ ደም ይሆናል፤ ከዚያም በተመሳሳይ የቀናት ብዛት ቁራጭ ስጋ ይሆናል፤ ከዚያም ወደርሱ መልዐክ ይላካለትና ነፍስም በውስጡ ይነፋበታል፤ መልዐኩ አራት መልእክቶች እንዲያሰፍር ይታዘዛል፤ ሲሳዩን፣ የሞት ቀጠሮውን፣ ስራውንና እድለቢስ ወይም እድለኛ መሆኑን ይጽፋል። ከርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ በሌለው በአላህ እምላለሁ! አንዳችሁ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የጀነት ሰዎችን ስራ እየሰራ ይቆይና በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ውሳኔ) ቀድሞት የእሳት ባለቤቶችን ስራ በመስራት እሳት ይገባል። አንዳችሁም በርሱና በእሳት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የእሳት ሰዎችን ስራ እየሰራ ይቆይና በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ውሳኔ) ቀድሞት የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [رواه البخاري ومسلم] - [الأربعون النووية - 4]

ትንታኔ

ኢብኑ መስዑድ እንዲህ አለ፦ በንግግራቸው እውነተኛ የሆኑትና አላህ እውነተኛነታቸውን በማረጋገጡ እውነተኛ የተባሉት የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነገሩን: ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦ "አንዳችሁ ፍጥረቱ ይሰበሰባል" ይህም አንድ ወንድ ባለቤቱን የተገናኘ ጊዜ የተበታተነው ዘር ፈሳሹ በሴቷ ማህጸን ውስጥ ለአርባ ቀን የዘር ፈሳሽ ሆኖ ይሰበሰባል። ከዚያም የረጋ ደም ይሆናል። ይህም የደረቀ ወፍራም ደም ነው። ይህ በሁለተኛው አርባ የሚከሰት ነው። ከዚያም ቁራጭ ስጋ ይሆናል። ይህም የሚታኘክ የሚያህል ቁራጭ ስጋ ነው። ይህ በሶስተኛው አርባ የሚከሰት ነው። ከዚያም ወደርሱ አላህ መልዐክ ይልካል። ሶስተኛው አርባ ከተጠናቀቀ በኋላ ፅንሱ ውስጥ ሩሕ (ነፍስ) ይነፋበታል። መልዐኩ አራት መልእክቶችን እንዲጽፍ ይታዘዛል። እነሱም:- ሲሳዩን: ይህም በእድሜው ውስጥ ምን ያህል መጠን ነው የሚያገኘው ፀጋ የሚለውን ነው። የሞት ቀጠሮውን:- ይህም በዱንያ ውስጥ የሚቆይበትን ዘመን ነው። ሥራውን:- ምንድነው እሱ? እድለቢስ ነው ወይስ እድለኛ? ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ማሉ። አንዱ የጀነት ሰዎችን ሥራ ይሠራል፤ ሥራው ለሰዎች በሚታየው መልካም ይሆናል፤ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል እስኪቀር በዚው መልክ ይቀጥላል። ማለትም አንድ ያሰበው ቦታ ለመድረስ አንድ ክንድ እንደቀረው ሰው በርሱና ጀነት በመግባት መካከልም አንድ ክንድ በስተቀር ምንም አይቀርም። በርሱ ላይ የተወሰነው መጽሐፉ ይቀድምና በዛን ወቅት የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራና በዛው ላይ ፍፃሜው ይሆናል። እሳትም ይገባል። ሥራ ተቀባይነት እንዲያገኝ አንዱ መስፈርት በዛው ላይ መፅናትና አለመለወጥ ነውና። ከሰዎች ሌላኛው ደግሞ እሳት ለመግባት በርሱና በእሳት መካከል የምድር አንድ ክንድ ያህል የቀረው እስኪመስል ድረስ የእሳት ባለቤቶችን ሥራ ይሠራል፤ በርሱ ላይ የተወሰነው መጽሐፉ ይቀድምና የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሰዎች አፈጣጠር እርከኖች መገለፁን እንረዳለን።
  2. በአላህ ቅድመ ውሳኔና ፍርድ ማመንን እንረዳለን።
  3. የነገሮች ፍፃሜ መዳረሻቸው በቀደመው ውሳኔና በተፃፈው ፍርድ መሰረት ነው።
  4. ሥራዎች የሚለኩት በፍፃሜያቸው ስለሆነ በሥራዎች ይዘት ከመሸወድ ማስጠንቀቅን ተረድተናል።
  5. ____
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري Kannadisht الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ