عَنْ أُمِّ المُؤْمِنِينَ أُمِّ عَبْدِ اللَّهِ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا، قَالَتْ: قَالَ: رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم:
«مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ فَهُوَ رَدٌّ».
وَفِي رِوَايَةٍ لِمُسْلِمٍ: «مَنْ عَمِلَ عَمَلًا لَيْسَ عَلَيْهِ أَمْرُنَا فَهُوَ رَدٌّ».
[صحيح] - [رواه البخاري ومسلم] - [الأربعون النووية: 5]
المزيــد ...
የአማኞች እናት፣ የዐብደላህ እናት ከሆነችው ከዐኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"በዚህ ጉዳያችን ከእርሱ ያልሆነን አዲስ ነገር ያመጣ ይዞት የመጣው አዲስ ፈሊጥ ውድቅ ነው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [رواه البخاري ومسلم] - [الأربعون النووية - 5]
በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ነገር የፈጠረ ወይም ቁርአናዊና ሐዲሣዊ ማስረጃ ያልጠቆሙትን ስራ የሰራ ሰው በባለቤቱ ላይ ተመላሽ እንደሚሆንና አላህ ዘንድም ተቀባይነት እንደማይኖረው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።