ምድቡ:
+ -


____

[] - []
المزيــد ...

ከአቡ ዐብደላህ ኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
"ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። በመካከላቸው አብዛኛው ሰዎች የማያውቃቸው አሻሚ ጉዳዮች አሉ። አሻሚ ጉዳዮችን የተጠነቀቀ ሰው ሃይማኖቱንና ክብሩን ጠብቋል። አሻሚ ጉዳዮች ላይ የወደቀም ሰው ሐራም ላይ ወድቋል። የዚህ ሰው አምሳያ ልክ የተከለከለ ክልል ወሰን ዙሪያ እንደሚጠብቅና እንስሳዎቹም ወሰን አልፈው የተከለከለው ክልል ውስጥ ሊገቡ እንደቀረቡበት እረኛ ነው። አዋጅ! ለሁሉም ንጉስ ወሰን (ድንበር) አለው። አዋጅ! የአላህ ወሰን (ድንበር) ደግሞ ክልከላው ነው። አዋጅ! ሰውነት ውስጥ የምትገኝ ቁራጭ ስጋ አለች። እሷ ከተስተካከለች ሁሉም ሰውነት ይስተካከላል። እሷ ከተበላሸች ደግሞ ሁሉም ሰውነት ይበላሻል። አዋጅ! እሷም ልብ ናት።"

[ሶሒሕ ነው።] - [رواه البخاري ومسلم] - [الأربعون النووية - 6]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለነገሮች ሁሉ የሚያገለግል አጠቃላይ መርህን እያብራሩ ነው። ነገሮች ሁሉ በሸሪዐ መሰረት ወደ ሶስት ክፍሎች ይከፈላሉ: ግልፅ ሐላል ፣ ግልፅ ሐራምና ከፍቁድነትና ክልክልነት አንፃር ብዙ ሰው ብይናቸውን የማያውቃቸው ግልፅ ያልሆኑ አሻሚ ጉዳዮች ናቸው።
በሱ ላይ አሻሚ የሆኑበትን ጉዳዮች የተወ ሰው ሀራም ላይ ከመውደቅ በመራቁ ሳቢያ እምነቱ ሰላም ይሆናል፤ ይህን አሻሚ የሆነ ጉዳይ በመፈፀሙ ሳቢያ እሱ ላይ የሚደርስን የሰዎች ትችት ስለማይኖርም ክብሩ ከትችት ሰላም ይሆናል። አሻሚ ጉዳዮችን ያልራቀ ሰው ግን ወይ ሐራም ላይ በመውደቅ ወይ በሰዎች ክብሩ በመዘለፉ ሳቢያ ነፍሱን (ለችግር) ያጋልጣታል። መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አሻሚ ጉዳዮች የሚፈፅምን ሰው ሁኔታ ለማብራራት ምሳሌ ጠቀሱ። እሱም ልክ ባለቤቱ በከለላት ስፍራ አስጠግቶ ከብቶቹን እንደሚያሰማራ እረኛ ነው። ቀስ በቀስ የእረኛው ከብቶች ወደተከለለው ስፍራ ቅርብ ስለሆኑ ክልሉ ውስጥ ዘልቀው ሊበሉ ይቀርባሉ። ልክ እንደዚሁ አሻሚ የሆኑ ጉዳዮችን የሚሰራ ሰው በዚህ መዳፈሩ ሳቢያ ወደ ሐራም ይቃረባል። ቀስበቀስ ሐራም ውስጥ ሊወድቅም ይቀርባል። ቀጥለውም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰውነት ውስጥ የምትገኝ ቁራጭ ስጋ እንዳለች ገለፁ። (እሷም ልብ ናት።) በሷ መስተካከል ሰውነት ይስተካከላል በሷ መበላሸትም ሰውነት ይበላሻል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ይህ ሐዲሥ ተመሳሳይ (የሚያምታቱ) የሆኑ ነገሮችን ለመጠንቀቅ መርህ የሆነ ሐዲሥ ነው።
  2. ብይናቸው ግልፅ ያልሆኑ አሻሚ ጉዳዮችን መተው መበረታታቱን እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأكانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ