ምድቡ:
+ -

عَنْ أَبِي رُقَيَّةَ تَمِيمِ بْنِ أَوْسٍ الدَّارِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«الدِّينُ النَّصِيحَةُ» قُلْنَا: لِمَنْ؟ قَالَ: «لِلهِ وَلِكِتَابِهِ وَلِرَسُولِهِ وَلِأَئِمَّةِ الْمُسْلِمِينَ وَعَامَّتِهِمْ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [الأربعون النووية: 7]
المزيــد ...

ከአቡ ሩቀየህ ተሚም ቢን አውስ አድዳሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ፦
"ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።" እኛም "ለማን ነው (የምንቆረቆረው) ታማኝ የምንሆነው?" አልናቸው። እሳቸውም "ለአላህ፣ ለመጽሐፉ፣ ለመልክተኛው፣ ለሙስሊሞች መሪዎችና ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [الأربعون النووية - 7]

ትንታኔ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዲን የቆመው ስራን አላህ ግዴታ ባደረገው መልኩ ያለምንም ማጓደል ወይም ያለምንም ማታለል በመፈፀም ስራን ለአላህ በማጥራት (በኢኽላስ) እና በእውነተኝነት ላይ በመመርኮዝ መሆኑን ተናገሩ። ለነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ታማኝ (ተቋርቋሪ) የምንሆነው ለማን ነው?" ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም: የመጀመሪያው: ለአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስራን ለርሱ በማጥራት፣ በርሱ ባለማጋራት፣ በጌትነቱ በተመላኪነቱና በስሞቹና በባህሪያቶቹ በማመን፣ ትእዛዙን በማላቅና በርሱ ወደማመን በመጣራት ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ነው። ሁለተኛው: ለመፅሀፉ ታማኝ (ተቆርቋሪ) መሆን ነው። እርሱም የተከበረው ቁርአን ነው። ይህም ቁርአን የአላህ ንግግር መሆኑን፣ የመጨረሻ መፅሀፉ መሆኑን፣ ከቁርአን በፊት የነበሩትን ሁሉንም ህግጋት የሻረ መሆኑን ማመን፤ እናልቀዋለን፣ በአግባቡ እናነበዋለን፣ ግልፅ በሆኑ ህግጋቶቹ እንተገብራለን፣ አሻሚ ትርጓሜ ባላቸው አንቀጾች እናምናለን፣ ቁርአንን አጣመው ከሚተረጉሙ ሰዎች ስለቁርአን እንከላከላለን፣ በምክሮቹ እንገሰፃለን፣ እውቀቶቹን እናሰራጫለን፣ ወደርሱም ጥሪ እናደርጋለን። ሶስተኛው: ለመልክተኛው ሙሐመድ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ማለት እርሳቸው የመጨረሻ መልክተኛ መሆናቸውን በማመን፣ ይዘውት የመጡትን እውነት ብለን በመቀበል፣ ትእዛዛቸውን በመፈፀም፣ ክልከላቸውንም በመራቅ፣ እርሳቸው ይዘውት በመጡት መልኩ ካልሆነ በቀር አላህንም ባለማምለክ ሐቃቸውን ማላቅ፣ ማክበር፣ ጥሪያቸውን ማሰራጨት፣ ሸሪዓቸውን ማስፋፋትና እርሳቸው ላይ የሚነዛን ብዥታንም ውድቅ ማድረግ ነው። አራተኛው: ለሙስሊም መሪዎች ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ማለት: በሐቅ ላይ በማገዝ፣ በጉዳያቸው ባለመቀናቀን፣ አላህን በታዘዙበት ጉዳይም ትእዛዛቸውን በመስማትና በመታዘዝ ነው። አምስተኛው: ለሙስሊሞች ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ማለት: ለነርሱ በጎ በመዋል፣ ጥሪ በማድረግ፣ በነርሱ ላይ ጉዳት ከማድረስ በመቆጠብ፣ ለነርሱ መልካሙን በማሰብ፣ በመልካምና አላህን በመፍራት ላይም ከነርሱ ጋር በመተጋገዝ ነው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ለሁሉም (ቅን/ ታማኝ) መሆን መታዘዙን እንረዳለን።
  2. በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ (ቅን/ ታማኝ) የመሆን ደረጃ የላቀ መሆኑን እንረዳለን።
  3. የእስልምና ሃይማኖት እምነቶችን፣ ንግግሮችንና ተግባራቶችን ያጠቀለለ መሆኑን እንረዳለን።
  4. ከታማኝነት መካከል አንዱ ቅንነቱ ለተገባው አካል ከማታለል ነፍሳችንን ማፅዳትና ለሱ መልካምን መፈለግ ነው።
  5. መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድን ነገር በጥቅሉ አውስተው ከዚያም መዘርዘራቸው የሳቸውን የማስተማር ብቃታቸው ውበትን ይጠቁማል።
  6. ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለአላህ ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) በመሆን ጀምረው ከዚያም ለመጽሐፉ ከዚያም ለመልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዚያም ለሙስሊም መሪዎች ከዚያም ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) በመሆን ማጠቃለላቸው የትኛውም ነገር እጅግ አንገብጋቢ ከሆነው ጉዳይ ሊጀመር እንደሚገባው እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ