عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ صَخْرٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: سَمِعْت رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم يَقُولُ:
«مَا نَهَيْتُكُمْ عَنْهُ فَاجْتَنِبُوهُ، وَمَا أَمَرْتُكُمْ بِهِ فَافْعَلُوا مِنْهُ مَا اسْتَطَعْتُمْ، فَإِنَّمَا أَهْلَكَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ كَثْرَةُ مَسَائِلِهِمْ، وَاخْتِلَافُهُمْ عَلَى أَنْبِيَائِهِمْ».
[صحيح] - [رواه البخاري ومسلم] - [الأربعون النووية: 9]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ ዐብዱራሕማን ቢን ሶኽር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
"የከለከልኳችሁን ነገር ራቁ፤ ካዘዝኳችሁም ነገር የቻላችሁትን ያህል ፈፅሙ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው ጥያቄ ማብዛታቸውና ነቢያቶቻቸውን መቃረናቸው ነው።"»
-
የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንድ ነገር የከለከሉን ጊዜ ያለምንም መለየት ሁሉንም ክልከላዎች መራቅ በኛ ላይ ግዴታ እንደሆነና አንድ ነገር ያዘዙን ጊዜ ደግሞ የምንችለውን ያህል መስራት በኛ ላይ ግዴታ እንደሆነ ገለፁልን። ቀጥለውም እንደአንዳንድ የቀደሙ ህዝቦች አይነት አጠፋፍ እንዳንጠፋ አስጠነቀቁን። እነዚህ የቀደሙ ህዝቦች ነቢያቶቻቸውን በመቃረናቸውምና ጥያቄዎችን በማብዛታቸው አላህ በጥፋትና ውድመት አይነት ቀጣቸው። ስለዚህ እነርሱ እንደጠፉት እንዳንጠፋ እነደነርሱ ከመሆን መራቅ ይገባናል።