عن أبِي هُرَيرةَ رضي الله عنه أنَّ رسول الله صلى الله عليه وسلمَ قال:
«إذا قُلْتَ لِصَاحِبِكَ: أَنْصِتْ، يومَ الجمعةِ، والْإِمامُ يَخْطُبُ، فَقَدْ لَغَوْتَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 851]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 851]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የጁሙዓ ኹጥባ ላይ የተሳተፈ ሰው ሊያሟላቸው ከሚገባ ግዴታ ስርዐቶች መካከል ተግሳፁን ሊያስተነትን ዘንድ ኹጥባ አድራጊውን በጥሞና ማዳመጥ እንደሚገባ ግልፅ አደረጉ። ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለሌላ ሰው "ዝም በል!" "አዳምጥ!" እንደማለት ትንሽ ነገር እንኳ ያወራ ሰውም ቢሆን የጁመዐ ሶላት ትሩፋት አምልጦታል።