عن عثمان بن عفان رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ تَوَضَّأَ فَأَحْسَنَ الْوُضُوءَ خَرَجَتْ خَطَايَاهُ مِنْ جَسَدِهِ حَتَّى تَخْرُجَ مِنْ تَحْتِ أَظْفَارِهِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 245]
المزيــد ...
ከዑሥማን ቢን ዐፋን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 245]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ውዱእን ሱናዎቹና አዳቦቹን ከመጠባበቅ ጋር ያደረገ ሰው ይህ ውዱኡ ወንጀሎቹ ከእጆቹና እግሮቹ ጣቶች ስር ጭምር እስኪወጡ ድረስ ወንጀሎቹ እንዲማሩና ሀጢአቶቹ እንዲረግፉ ከሚያደርጉ ምክንያቶቹ አንዱ መሆኑን እየነገሩን ነው።