عن عائشة رضي الله عنها قالت: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«السِّوَاكُ مَطْهَرَةٌ لِلْفَمِ، مَرْضَاةٌ لِلرَّبِّ».

[صحيح] - [رواه النسائي وأحمد]
المزيــد ...

ዓኢሻህ ረዲየሏሁ ዐንሀ እንዲህ ማለቷ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡
'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'"

ሶሒሕ ነው። - [An-Nasaa’i]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አራክ በተባለው ወይም በአምሳያው በሆነ መፋቂያ ጥርስን መፋቅ አፍን ከቆሻሻ እና ከመጥፎ ጠረን እንደሚያፀዳ ነገሩን። ይህንኑ ማድረግም ለአሏህ ታዛዥነትና ለትእዛዙ ምላሽ መስጠት ከመሆኑ ባሻገር አሏህ የሚወደውን ንፅህናንም የሚያስተርፍ ስለሆነ ድርጊቱ የአሏህን ውዴታ ማግኛ ሰበብ መሆኑን ነገሩን።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ጥርስን መፋቅ ያለውን ትሩፋትና ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ዑመታቸው ድርጊቱን ያበዛ ዘንድ ማነሳሳታቸውን እንረዳለን።
  2. ቢፍቁበት የተሻለው "አራክ" የተባለውን የዛፍ ግንድ (መፋቂያ) ከመሆኑም ጋር በምትኩ የጥርስ ብሩሽ ከሳሙናው ጋር መጠቀምም ይቻላል።