+ -

عَنْ عَائِشَةَ رضي الله عنها قَالَتْ:
قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ، ابْنُ جُدْعَانَ كَانَ فِي الْجَاهِلِيَّةِ يَصِلُ الرَّحِمَ، وَيُطْعِمُ الْمِسْكِينَ، فَهَلْ ذَاكَ نَافِعُهُ؟ قَالَ: «لَا يَنْفَعُهُ، إِنَّهُ لَمْ يَقُلْ يَوْمًا: رَبِّ اغْفِرْ لِي خَطِيئَتِي يَوْمَ الدِّينِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 214]
المزيــد ...

የምእመናን እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንዲህ ብላለች፦
"የአላህ መልክተኛ ሆይ! ኢብኑ ጁድዓን በጃሂሊያ (በድንቁርናው)ዘመን ዝምድናን የሚቀጥልና ሚስኪኖችን የሚመግብ ነበር። ይህ ይጠቅመዋልን?" አልኳቸው። እሳቸውም "አንድ ቀንም "ጌታዬ ሆይ! የምንዳው ቀን ወንጀሎቼን ማረኝ" ብሎ ስለማያውቅ አይጠቅመውም።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 214]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከእስልምና በፊት የቁረይሽ ሹማምንቶች መካከል ስለነበረው ዐብደላህ ቢን ጁድዓን ተናገሩ። ከመልካም ሥራዎቹ መካከልም፦ ዝምድናውን የሚቀጥል፣ ለነሱ መልካም የሚሰራ፣ ሚስኪኖችን የሚመግብና ሌሎችም እስልምና እንዲተገበር ያነሳሳቸውን መልካም ስራዎች የሚሰራ ነበር። እነዚህ ተግባሮቹ ግን በአላህ በመካዱና አንድ ቀንም "ጌታዬ ሆይ! የምንዳው ቀን ለኔ ወንጀሎቼን ማረኝ" ባለማለቱ ምክንያት ለመጪው ዓለም አትጠቅመውም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የኢማን ትሩፋትና ስራዎች ተቀባይነት እንዲያገኙ መስፈርት እንደሆነ መገለፁ።
  2. የክህደት መጥፎነትና መልካም ስራዎችን የሚያበላሽ እንደሆነ መብራራቱ።
  3. ከሀዲያን በአላህና በመጨረሻው ቀን ስለማያምኑ በመጪው ዓለም ሥራዎቻቸው አይጠቅማቸውም።
  4. የሰው ልጅ በክህደት ዘመኑ የሠራቸው መልካም ስራዎች በሚሰልም ወቅት የሚጻፍለትና በመልካም ስራዎቹ የሚመነዳ መሆኑን ፤
ተጨማሪ