عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«قَالَ اللهُ: أَنْفِقْ يَا ابْنَ آدَمَ أُنْفِقْ عَلَيْكَ».
[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'"
ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከፍ ያለውና የላቀው አላህ "የአደም ልጅ ሆይ! ግዴታም ይሁን ተወዳጅ የሆኑብህን ወጪዎች ለግስ! ላንተም ሲሳይን አሰፋልሃለሁ፣ ያዋጣኸውን ወጪ ልውጫ እሰጥሃለሁ፣ በሰጠሁህም ነገር ላንተ እባርክልሃለሁ" ማለቱን ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።