عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما قال:
سَمِعَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ رَجُلًا يَعِظُ أَخَاهُ فِي الْحَيَاءِ، فَقَالَ: «الْحَيَاءُ مِنَ الْإِيمَانِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 36]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ሰውዬ ወንድሙን በአይነአፋርነቱ ሲወቅሰው ሰሙና 'አይነአፋርነት ከኢማን ነው።' አሉት።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 36]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድን ሰውዬ ለወንድሙ አይነአፋርነት ማብዛት እንዲተው ሲመክረው ሰሙትና አይነአፋርነት ከኢማን መሆኑን እና ከመልካም በስተቀር ይዞ እንደማይመጣ ገለፁለት።
አይነአፋርነት መልካም ድርጊት ለመስራትና እኩይ ተግባር ለመተው የሚያነሳሳ ስነምግባር ነው።