عن أبي مسعود الأنصاري رضي الله عنه قال:
جَاءَ رَجُلٌ إِلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ: إِنِّي أُبْدِعَ بِي فَاحْمِلْنِي، فَقَالَ: «مَا عِنْدِي»، فَقَالَ رَجُلٌ: يَا رَسُولَ اللهِ، أَنَا أَدُلُّهُ عَلَى مَنْ يَحْمِلُهُ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1893]
المزيــد ...
ከአቡ መስዑድ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:
አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "መንገድ ተቋርጦብኛልና የምጓጓዝበት እንስሳ ይስጡኝ?" አላቸው። እሳቸውም "የለኝም!" አሉት። ሌላ ሰውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ መጓጓዣ የሚሰጠውን እጠቁመዋለሁ!" አለ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1893]
አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "እኔ ግመሌ ስለጠፋች የሚያደርሰኝን አንድ መጓጓዣ ይስጡኝ!" አላቸው። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እሳቸው የሚሰጡት ምንም ነገር እንደሌለ ነገሩት። እሳቸው ዘንድ የነበረ አንድ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ የሚሰጠውን ሰው እጠቁመዋለሁ።" አለ። የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምፅዋት ፈላጊን ለሚመፀውተው አካል በመጠቆሙ ምክንያት ከሚመፀውተው ሰው ጋር በአጅር እንደሚጋራ ተናገሩ።