+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«السَّاعِي عَلَى الأَرْمَلَةِ وَالمِسْكِينِ، كَالْمُجَاهِدِ فِي سَبِيلِ اللَّهِ، أَوِ القَائِمِ اللَّيْلَ الصَّائِمِ النَّهَارَ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5661]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
‹ባሏ ለሞተባትና ለሚስኪን የሚለፋ ሰው ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ሰው አምሳያ ወይም ልክ ሌሊት እየሰገደ ቀኑን እንደሚፆም አምሳያ ነው›"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5661]

ትንታኔ

ባሏ ለሞተባትና የሚያስፈልጋትን ጉዳይ የሚያሟላላት አንድም ሰው ለሌላት ሴት እና ተረጂ ለሆነ ሚስኪን ጥቅማቸውን በሟሟላት የቆመ እንዲሁም አላህ ዘንድ ምንዳን በማሰብ ለነርሱ ወጪ የሚያደርግ ሰው በምንዳ ደረጃ ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ወይም ለተሀጁድ ሶላት ሳይደክም እየቆመ ምንም ሳያፈጥር እንደሚፆም ሰው አምሳያ መሆኑን ነቢዩ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በመተጋገዝ፣ ሀላፊነት በመወጣትና የደካሞችን አስፈላጊ ጉዳዮች በማሟላት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. አምልኮ ሲባል ሁሉንም መልካም ስራ ይሰበስባል። ከአምልኮዎች መካከልም ባሏ ለሞተባት ሴትና ለሚስኪን ጥቅም መልፋት አንዱ ነው።
  3. ኢብኑ ሁበይራ እንዲህ ብሏል: "ከዚህ ሐዲሥ የተፈለገው ከፍ ያለው አላህ የታጋይ (የሙጃሂድ)ና እየፆመ ሌሊት የሚቆምን ሰው ምንዳ በአንድ ጊዜ ይሰበስብለታል ማለት ነው። ይህም ባሏ ለሞተባት ሴት የባሏን ቦታ ተክቶ ስለተወጣ … ራሱን ችሎ መቆም ለተሳነው ሚስኪንም የተረፈውን ቀለብ ወጪ አድርጎ በአቅሙ ስለመፀወተ የሰጠው ጥቅም ፆም፣ የሌሊት ሶላትና ጂሀድን የሚመጥን ሆነ።"