عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ يَقُمْ لَيْلَةَ الْقَدْرِ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ»
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 35]
المزيــد ...
አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 35]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በረመዳን ከመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ የምትገኘው መወሰኛይቱ ሌሊትን (ለይለቱል ቀድርን) የመቆም ትሩፋትን ተናገሩ። በዚህች ሌሊት በሷና ስለሷ ትሩፋት በመጡ ሐዲሦች አምኖ እንዲሁም በስራው ይዩልኝና ይስሙልኝን ሳይሆን የአላህን ምንዳ ከጅሎ በሶላት፣ በዱዓእ፣ ቁርአን በመቅራትና በዚክር የታገለ ሰው ያለፈውን ኃጢዓቱ ይማራል።