عن عثمان رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«خَيْرُكُمْ مَنْ تَعَلَّمَ الْقُرْآنَ وَعَلَّمَهُ».
[صحيح] - [رواه البخاري]
المزيــد ...
ከዑስማን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።"
ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪ ዘግበውታል።
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሙስሊሞች መካከል በላጩና አላህ ዘንድ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ቁርአን ማንበብን፣ መሸምደድን፣ ማሳመርን፣ መገንዘብንና ማብራራትን የተማረና እርሱ ዘንድ ያለውን የቁርአን እውቀት ከመተግበሩም ጋር ለሌላው ያስተማረ መሆኑን ተናገሩ።