عن عمر بن الخطاب رضي الله عنه قال: إنه سمع نبي الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«لَو أَنَّكُمْ تَتَوَكَّلُونَ عَلَى اللهِ حَقَّ تَوَكُّلِهِ، لَرَزَقَكُمْ كَمَا يَرْزُقُ الطَّيْرَ، تَغْدُو خِمَاصًا وَتَرُوحُ بِطَانًا».

[صحيح] - [رواه الترمذي وابن ماجه وأحمد]
المزيــد ...

ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማ:
"በአላህ ላይ ትክክለኛውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚለግሰው ለናንተም ሲሳይን ይለግሳቹህ ነበር። (ወፍ) ተርባ ማልዳ ትወጣለች። ሆዷ (በጥጋብ) ሞልቶ ትመለሳለች።"

Sahih/Authentic. - [Ibn Maajah]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዱንያዊም በዲናዊም ጉዳይ ጥቅምን በማምጣትና ጉዳትን በመከላከል ረገድ በአላህ ላይ እንድንደገፍ እያነሳሱን ነው። ምክንያቱም ከአላህ በስተቀር የሚሰጥም፣ የሚከለክልም ፣ የሚጎዳም፣ የሚጠቅምም የለምና ነው። ጥቅሞችን የሚያመጡና ጉዳቶችን የሚከላከሉ ሰበቦችን በአላህ ላይ ከእውነተኛ መመካት ጋር እንድንፈፅምም አነሳሱ። ይህንን በማንኛውም ወቅት ከፈፀምን አላህ ወፍን በንጋት የተራበች ሆና ወጥታ ከዚያም በምሽት ሆዷ ሞልቶ በመመለስ እንደሚቀልባት እኛንም ይቀልበን ነበር። ይህ የወፏ ድርጊት ያለመሳነፍና መዳከም ሲሳይን ለመፈለግ የሰራችው የሰበብ አይነት ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የመመካት ትሩፋትን ፤ መመካት ሲሳይን ከሚያመጡ መንስኤዎች መካከል ትልቁ ነው ።
  2. መመካት ሰበቦችን ከመፈፀም ጋር አይጋጭም። ምክንያቱም እሳቸው ሲሳይ ለመፈለግ ማልዶ መውጣትና አምሽቶ መመለስ ትክክለኛውን መመካት እንደማይጣረሰው ተናግረዋልና።
  3. ሸሪዐ ለቀልብ ተግባራት ትኩረት መስጠቱን፤ መመካት የቀልብ ተግባር ነውና።
  4. በሰበብ ላይ ብቻ መንጠልጠል የዲን ጉድለት ሲሆን ሰበቦችን መተው ደግሞ የአይምሮ ጉድለት ነው።