عَنْ المُغِيرَةِ رضي الله عنه قَالَ:
كُنْتُ مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي سَفَرٍ، فَأَهْوَيْتُ لِأَنْزِعَ خُفَّيْهِ، فَقَالَ: «دَعْهُمَا، فَإِنِّي أَدْخَلْتُهُمَا طَاهِرَتَيْنِ» فَمَسَحَ عَلَيْهِمَا.

ከሙጊራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:
"አንድ ጉዞ ላይ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩና ኹፋቸውን (የቆዳ ካልሲያቸውን) ላወልቅ ዝቅ አልኩ፤ እሳቸውም: ' እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።' አሉኝና በነርሱ ላይ አበሱ።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 206

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአንድ ጉዟቸው ላይ ሳሉ ዉዱእ አደረጉ። ሁለት እግራቸውን ማጠብ ላይ በደረሱ ጊዜ ሙጊራ ቢን ሹዕባ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እግራቸውን እንዲያጥቡ ብለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አድርገውት የነበረውን ኹፍ ሊያወልቁ እጃቸውን ዘረጉ ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "አታውልቃቸው ተዋቸው! እኔ ሁለት እግሬን ኹፎቹ ውስጥ ያስገባሁት በጦሀራ ላይ ሁኜ ነው " አሏቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እግራቸውን በማጠብ ምትክ ኹፋቸውን አበሱ።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ሁለት ኹፎች ላይ ማበስ የተደነገገው ከትንሹ ሐደሥ (ዉዱእ አጥፍቶ) ዉዱእ በሚደረግበት ወቅት ነው። ለትልቁ ሐደሥ (ገላን ለሚያስታጥብ ጉዳይ) መታጠብ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ግን የግድ ሁለት እግሮችን መታጠብ ይኖርበታል።
  2. ኹፍ ላይ ማበስ የሚፈፀመው በውሃ በረጠበ እጅ ታችኛውን ሳይሆን ላይኛውን የኹፉ ክፍል አንድ ጊዜ በመዳበስ ነው።
  3. በሁለት ኹፎች ላይ ለማበስ ሊሟሉ የሚገቡ መስፈርቶች አሉ። እነሱም: ኹፎቹን የሚለብሰው ሁለት እግሮቹን በውሃ ካጠበበት የተሟላ ዉዱእ በኋላ መሆን ይገባዋል፤ ኹፉ ንፁህና በትጥበት ወቅት ማጠብ ግዴታ የሆነውን የእግሩን ክፍል የሸፈነ መሆን ይገባዋል፤ የሚያብሰው በጀናባ (የዘር ፈሳሽ መጥቶት ወይም ግንኙነት በማድረጉ) ወይም ገላን የሚያስታጥቡ ነገሮች ሲያጋጥሙት ሳይሆን በትንሹ ሐደሥ (ውዱእ የሚያስደርጉ ምክንያቶች ሲያጋጥሙት) ብቻ መሆን ይገባዋል፤ የሚያብሰውም በሸሪዓ በተወሰነው ወቅት መሆን ይገባዋል። እሱም መንገደኛ ላልሆነ አንድ ቀን ከነምሽቱ ሲሆን ጉዞ ላይ ላለ ደግሞ ሶስት ቀን ከነሌሊቱ ነው።
  4. እንደካልሲና የመሳሰሉት ሁለት እግሮችን የሚሸፍኑ ሁሉ እንደ ሁለቱ ኹፎች ተመሳሳይ ፍርድ ስላላቸው በነርሱም ላይ ማበስ ይበቃል።
  5. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙጊራ ኹፋቸውን እንዳያወልቅ ሲከለክሉት ነፍሱ እንድትረጋጋና ብይኑን እንዲያውቅ ምክንያታቸውን መግለፃቸው የርሳቸው ስነምግባርና የማስተማር መንገዳቸው ማማሩን ያስረዳናል።

ትርጉሞችን አሳይ

58 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
FR Français الفرنسية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
KMR Kurmancî الكرمنجية