عن عمران بن حصين رضي الله عنه قال: كَانَتْ بِي بَوَاسِيرُ، فَسَأَلْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ الصَّلَاةِ، فَقَالَ:
«صَلِّ قَائِمًا، فَإِنْ لَمْ تَسْتَطِعْ فَقَاعِدًا، فَإِنْ لَمْ تَسْتَطِعْ فَعَلَى جَنْبٍ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 1117]
المزيــد ...
ከዒምራን ቢን ሑሰይን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ኪንታሮት ነበረብኝና ስለ አሰጋገዴ ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠየቅኳቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉኝ:-
'ቁመህ! ካልቻልክ ተቀምጠህ ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ። '"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1117]
መቆም ባልተቻለበት ወቅት ካልሆነ በቀር ለሶላት አሰጋገድ መሰረቱ መቆም እንደሆነና መቆም ካልቻለ ተቀምጦ እንደሚሰግድ ተቀምጦ መስገድም ካልቻለ በጎኑ ተጋድሞ መስገድ እንደሚችል ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ።