عن عبد الله بن عمرو رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«بَلِّغُوا عَنِّي وَلَوْ آيَةً، وَحَدِّثُوا عَنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَلَا حَرَجَ، وَمَنْ كَذَبَ عَلَيَّ مُتَعَمِّدًا فَلْيَتَبَوَّأْ مَقْعَدَهُ مِنَ النَّارِ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 3461]
المزيــد ...
ከዐብደሏህ ቢን ዐምር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"አንዲትም አንቀጽ ቢሆን ከኔ አስተላልፉ። ከቤተ እስራኤላውያንም አውሩ ችግር የለውም። ሆን ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ከእሳት የሆነን መቀመጫውን ያመቻች።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3461]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከርሳቸው የተማርነውን ቁርአናዊም ይሁን ሐዲሣዊ እውቀት አንድ አንቀፅ ያህል ትንሽ እንኳ ቢሆን እንድናስተላልፈው አዘዙን፤ ይህም ግን የምንጣራበትንና የምናደርሰውን መልእክት ተረድተነው መሆኑ ቅድመ መስፈርቱ ነው። ከዚያም ሽሪዓችን ጋር እስካልተጋጨ ድረስ ከበኒ ኢስራኢሎች የተከሰተባቸውን ክስተትና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ ማውራታችንም ችግር እንደሌለው ገለፁ። ከዚያም በሳቸው ላይ ከመቅጠፍ አስጠነቀቁ፤ ሆን ብሎ በሳቸው ላይ የዋሸም ጀሀነም ውስጥ ማረፊያውን እንዲይዝ አሳሰቡ።