ምድቡ:
+ -

عَنْ أَبِي نَجِيحٍ العِرْبَاضِ بْنِ سَارِيَةَ رضي الله عنه قَالَ: وَعَظَنَا رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مَوْعِظَةً وَجِلَتْ مِنْهَا القُلُوبُ، وَذَرَفَتْ مِنْهَا العُيُونُ، فَقُلْنَا: يَا رَسُولَ اللهِ! كَأَنَّهَا مَوْعِظَةُ مُوَدِّعٍ؛ فَأَوْصِنَا، قَالَ:
«أُوصِيكُمْ بِتَقْوَى اللَّهِ، وَالسَّمْعِ وَالطَّاعَةِ، وَإِنْ تَأَمَّرَ عَلَيْكُمْ عَبْدٌ، فَإِنَّهُ مَنْ يَعِشْ مِنْكُمْ بَعْدِي فَسَيَرَى اخْتِلَافًا كَثِيرًا، فَعَلَيْكُمْ بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الخُلَفَاءِ الرَّاشِدِينَ المَهْدِيينَ، عَضُّوا عَلَيْهَا بِالنَّوَاجِذِ، وَإِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الأُمُورِ؛ فَإِنَّ كُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ».

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي] - [الأربعون النووية: 28]
المزيــد ...

ከአቡ ነጂሕ ዒርባድ ቢን ሳሪየህ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ልቦናዎች የራዱበትና አይኖች ያነቡበትን ምክር መከሩን። እኛም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምክሮት ልክ የተሰናባችን ምክር ይመስላል። ምከሩን!" አልናቸው። እርሳቸውም:
"አላህን በመፍራት፤ ባሪያ እንኳ ቢሾምባችሁ እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። እነሆ! ከናንተ መካከል ከኔ በኋላ የሚኖር ሰው ብዙ ልዩነትን ማየቱ አይቀርም፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን በማኘኪያ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! ሁሉም ቢድዓ (አዲስ መጤ) ጥመት ነውና።" አሏቸው።»

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [الأربعون النووية - 28]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሐቦችን ልቦች በርሷ ምክንያት የራዱበትና ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰ ምክር መከሩ። ሰሐቦችም የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምክራቸው ጥግ የደረሰ መሆኑን ስላዩ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምክሮት የተሰናባች ምክር ትመስላለች።" በማለት ከርሳቸው ህልፈት በኋላ አጥብቀው የሚይዙትን አደራ ጠየቁ። እርሳቸውም "አላህን በመፍራት አደራ እላቹኃለሁ።" አሉ። ይህም ግዴታዎችን በመፈፀምና ክልክሎችን በመተው ነው። "ባሪያ በናንተ ላይ ቢሾም ወይም መሪ ሆኖ ቢመጣባችሁ እንኳ ለመሪዎች መስማትና መታዘዝን አደራ እላችኃለሁ።" ማለትም በናንተ ላይ ደረጃው የወረደ (አርጋችሁ የምታስቡት) ፍጡር መሪ ቢሆን እንኳ ፈተና ይቀጣጠላል ተብሎ ስለሚሰጋ በዚህ ላይ እምቢተኛ አትሁኑ ታዘዙት ማለት ነው። "እነሆ ከናንተ መካከል የሚኖር ሰው ብዙ ልዩነትን ያያል።" ቀጥለውም ከዚህ ልዩነት መውጫውን ገለፁላቸው። እሱም የርሳቸውን ሱና(ፈለግ) እና ከርሳቸው በኋላ የተመሩ የሆኑት ቅን ምትኮቻቸውን ሱና አጥብቆ በመያዝ ነው። እነሱም: አቡ በከር አስሲዲቅ፣ ዑመር ቢን አልኸጧብ፣ ዑሥማን ቢን ዐፋንና ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ የሁሉንም መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ናቸው። አጥብቃችሁ የምትይዙትም በማኘኪያ ጥርስ ነክሶ እንደመያዝ ነው። በዚህም ለማለት የፈለጉት ሱናን በመያዝና በማጥበቅ ላይ መጠንከርን ለመጠቆም ነው። በሃይማኖት ውስጥ ከተፈበረኩ አዳዲስ መጤ ጉዳዮችም አስጠነቀቋቸው። ሁሉም አዲስ መጤ ነገር ጥመት ነውና።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሱናን አጥብቆ መያዝና ሱናን መከተል አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ለምክሮችና ልቦችን ለሚያለሰልሱ ነገሮች ትኩረት መስጠት እንደሚገባ እንረዳለን።
  3. ከርሳቸው በኋላ ያሉት አራቱ የተመሩ ቅን ምትኮቻቸውን መከተል መታዘዙን እንረዳለን። እነሱም አቡ በከር፣ ዑመር፣ ዑሥማንና ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ናቸው።
  4. በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ነገር መፍጠር መከልከሉንና ሁሉም መጤ ነገር ጥመት መሆኑንም እንረዳለን።
  5. የአማኞችን ጉዳይ እንዲመራ ለተሾመ ሰው ከወንጀል ውጪ በሆኑ ጉዳዮች እርሱን መስማትና መታዘዝ እንደሚገባ እንረዳለን።
  6. አላህን በሁሉም ወቅትና ሁኔታ የመፍራትን አንገብጋቢነት እንረዳለን።
  7. በዚህ ኡመት ውስጥ ልዩነት ይከሰታል። በሚከሰት ወቅት ግን ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሱና እና ወደ ቅን ምትኮቻቸው ሱና መመለስ ግድ ይላል።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ