ምድቡ:
+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«كُلُّ سُلَامَى مِنَ النَّاسِ عَلَيْهِ صَدَقَةٌ، كُلَّ يَوْمٍ تَطْلُعُ فِيهِ الشَّمْسُ تَعْدِلُ بَيْنَ الِاثْنَيْنِ صَدَقَةٌ، وَتُعِينُ الرَّجُلَ فِي دَابَّتِهِ فَتَحْمِلُهُ عَلَيْهَا أَوْ تَرْفَعُ لَهُ عَلَيْهَا مَتَاعَهُ صَدَقَةٌ، وَالكَلِمَةُ الطَّيِّبَةُ صَدَقَةٌ، وَكُلُّ خُطْوَةٍ تَمْشِيهَا إِلَى الصَّلَاةِ صَدَقَةٌ، وَتُمِيطُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ صَدَقَةٌ».

[صحيح] - [رواه البخاري ومسلم] - [الأربعون النووية: 26]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሁሉም የሰው ልጅ መገጣጠሚያ አጥንቶች ምፅዋት አለባቸው። ፀሐይ በምትወጣበት ቀናት ሁሉ በሁለት ሰዎች መካከል ማስታረቅ ምፅዋት ነው፤ ሰውዬውን መጓጓዣው ላይ እንዲወጣ ማገዝ፣ እርሷ ላይ ማሸከም ወይም እቃውን እርሷ ላይ መጫን ምፅዋት ነው፤ መልካም ንግግር ምፅዋት ነው፤ ወደ ሶላት የምትራመዳት ሁሉም እርምጃ ምፅዋት ነው፤ ከመንገድ ላይ ቆሻሻን ማስወገድ ምፅዋት ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [رواه البخاري ومسلم] - [الأربعون النووية - 26]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁሉም ቀን በሁሉም ለአቅመ አዳም በደረሰ ሙስሊም ላይ ሁሉ በመገጣጠሚያ አጥንቶቹ ቁጥር ያህል አላህ ለሰጠው ጤንነት ለማመስገንና አጥንቶቹን መጨበጥና መዘርጋት በሚችል መልኩ ስለገጣጠመው ለአላህ ብሎ መመፅወት እንደሚገባው ገለፁ። ይህቺም ምፅዋት በመልካም ተግባራት ባጠቃላይ እንደሚፈፀምና ገንዘብ በመስጠት ላይ ብቻ እንዳልታጠረ ገለፁ። ከነርሱም መካከል: በተጣሉ ሁለት ሰዎች መካከል ማስታረቅና መፍረድ ምፅዋት ነው። መጓጓዣው ላይ ለመውጣት ለተሳነው ሰውዬ በማሰቀልህ ወይም እቃውን በመጫን ማገዝህ ምፅዋት ነው። ዚክር፣ ዱዓ ማድረግ፣ ሰላምታ ማቅረብና ሌሎችም መልካም ንግግሮች ምፅዋት ናቸው። ወደ ሶላት የምትራመዳት ሁሉም እርምጃ ምፅዋት ናት። መንገድ ላይ የሚያውክን ነገር ማስወገድም ምፅዋት ነው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሰው ልጅ አጥንቶች ተገጣጥመው መሰራታቸውና የነርሱም ደህና መሆን ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎች መካከል እንደሆነ እንረዳለን። ለያንዳንዱ ፀጋ የሚያቀርበው ምስጋና እንዲሞላም ለሁሉም አጥንት መመፅወት አስፈላጊ ነው።
  2. ይህ የአላህ ፀጋ እንዲዘወትርም ምስጋናን በየቀኑ በማደስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  3. በየቀኑ ግዴታ ያልሆኑ ስራዎችን በመስራትና ምፅዋት በማድረግ ላይ በመዘውተር መነሳሳቱን እንረዳለን።
  4. በሰዎች መካከል ማስታረቅ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
  5. ወንድምን በማገዝ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህም ወንድምን ማገዝ ምፅዋት ስለሆነ ነው።
  6. የጀመዓ ሶላት በመገኘት ላይ፣ ወደርሱ በመሄድ ላይና መስጂድ በመገኘት መስጂድን በማሳመር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  7. ሙስሊሞች የሚያውካቸውንና የሚጎዳቸውን ነገር በማራቅ የሙስሊሞችን መንገድ ማስከበር ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ