عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«قَالَ اللهُ تَبَارَكَ وَتَعَالَى: أَنَا أَغْنَى الشُّرَكَاءِ عَنِ الشِّرْكِ، مَنْ عَمِلَ عَمَلًا أَشْرَكَ فِيهِ مَعِي غَيْرِي تَرَكْتُهُ وَشِرْكَهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2985]
المزيــد ...
አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦ የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡
"የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ ' እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2985]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ማለቱን እየነገሩን ነው፡- አጋርን ከመፈለግ ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃው አሏህ ነው። እርሱም ከምንም የተብቃቃ ራሱን የቻለ ነው። አንድ ሰው መልካም ነገርን ሲያደርግ ለአላህም ለሌሎችም ብሎ ቢያደርገው አላህ ይህንን ስራውን ይተውለታል፤ አይቀበለውም፤ ወደራሱ ይመልስለታል። ስለዚህም ጥራት የተገባው አሏህ ጥርት ባለ መልኩ ለርሱ ተብሎ የተሰራውን መልካም ስራ ካልሆነ በቀር ሌላን ስራ ስለማይቀበል ኢኽላስን ለርሱ ማድረግ ግዴታ ነው።