عن أبي صِرْمة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ ضَارَّ ضَارَّ اللهُ بِهِ، وَمَنْ شَاقَّ شَقَّ اللهُ عَلَيْهِ».
[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن الترمذي: 1940]
المزيــد ...
ከአቡ ሲርመህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"የጎዳ ሰው አላህም ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀንም አላህም ያስጨንቀዋል።"
[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 1940]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነፍሱም ይሁን በገንዘቡም ይሁን በቤተሰቡም ይሁን በማንኛውም ጉዳዩ ላይ ሙስሊም ላይ ጉዳትና ችግርን ከማድረግ አስጠነቀቁ። ይህንንም ለፈፀመ አላህም በሰራው አምሳያ እንደሚመነዳውና እንደሚቀጣው ገለፁ።