+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«إِنَّ اللهَ لَا يَنْظُرُ إِلَى صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ، وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَالِكُمْ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2564]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወስለም እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2564]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ ወደ ሰዎች ቅርፅና ሰውነት ያምራል ወይስ አስቀያሚ? ትልቅ ወይስ ትንሽ? ጤነኛ ወይስ በሽተኛ? በማለት እንደማይመለከት ገለፁ። ወደ ገንዘቦቻቸውም ብዙ ወይስ ትንሽ? በማለት አይመለከትም። አላህ ባሮቹን በነዚህ ጉዳዮች ላይ ባላቸው መበላለጥ ተንተርሶ አይቀጣቸውምም አይተሳሰባቸውምም። ነገር ግን በቀልቦቻቸው ውስጥ ወዳለው ፍራቻ፣ የእምነት እርግጠኝነት፣ እውነተኝነት፣ ኢኽላስ (ፍፁማዊነት) ወይም የይዩልኝ ፣ የይስሙልኝ አስተሳሰብ ነው የሚመለከተው። ወደ ስራዎቻቸው ከመስተካከሏና ከመበላሸቷ አንፃር ይመለከትና በዛም መሰረት ይመነዳል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ቀልብን ከሁሉም ውግዝ ባህሪያት ማስተካከልና ማፅዳት ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለብን፤
  2. ቀልብ የሚስተካከለው በኢኽላስ ሲሆን ስራ የሚስተካከለው ደግሞ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመከተል ነው። አላህ ዘንድ ትኩረት የሚቸራቸውና ግምት ውስጥ የሚገቡት እነዚህ ሁለቱ ናቸው።
  3. የሰው ልጅ በገንዘቡም፣ በውበቱም፣ በሰውነቱም ሆነ በዚህች ዓለማዊ መገለጫዎች በአንዳችም ነገር መሸወድ እንደሌለበት ፤
  4. ውስጣዊ ማንነትን ሳያስተካክሉ ውጫዊ የሆኑ መገለጫዎችን ከመደገፍ መጠንቀቅ እንዳለብን ተረድተናል።
ተጨማሪ