1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ጥሪና ሰበካ

ሐዲሥ እነሆ በናንተ ላይ መሪዎች ይሾማሉ። የምታውቁትንም የምታወግዙትንም ስራ ይሰራሉ። (የሚሰሩትን ውግዝ ስራ) የጠላ ሰው (ከወንጀል) ጠራ። ያወገዘም ሰው ሰላም ሆነ። ነገር ግን (የነሱን ውግዝ ተግባር) የወደደና የተከተለ (ወንጀል ውስጥ ወደቀ)

عَنْ أُمِّ سَلَمَةَ أُمِّ المُؤمنين رضي الله عنها: أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ:
«سَتَكُونُ أُمَرَاءُ فَتَعْرِفُونَ وَتُنْكِرُونَ، فَمَنْ عَرَفَ بَرِئَ، وَمَنْ أَنْكَرَ سَلِمَ، وَلَكِنْ مَنْ رَضِيَ وَتَابَعَ» قَالُوا: أَفَلَا نُقَاتِلُهُمْ؟ قَالَ: «لَا، مَا صَلَّوْا».

ከኡሙ ሰለማ ኡሙል ሙእሚኒን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"እነሆ በናንተ ላይ መሪዎች ይሾማሉ። የምታውቁትንም የምታወግዙትንም ስራ ይሰራሉ። (የሚሰሩትን ውግዝ ስራ) የጠላ ሰው (ከወንጀል) ጠራ። ያወገዘም ሰው ሰላም ሆነ። ነገር ግን (የነሱን ውግዝ ተግባር) የወደደና የተከተለ (ወንጀል ውስጥ ወደቀ)" ሶሓቦችም "ታዲያ አንዋጋቸውምን?" ብለው ጠየቁ። ነቢዩም "ሶላትን እስከሰገዱ ድረስ በፍፁም (እንዳትዋጓቸው!)" ብለው መለሱ።

ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 1854

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኛ ላይ መሪዎች እንደሚሾሙና ከፊል ስራዎቻቸው ከሸሪዓ ጋር የተስማማ ስለሆነ መልካም እንደምንለውና፤ ከፊሉን ደግሞ ከሸሪዓ ጋር ስለሚፃረር እንደምናወግዘው ተናገሩ። ውግዝ ተግባሮቻቸውን ማውገዝ ያልቻለና በቀልቡ የጠላ ሰው በርግጥም ከወንጀልና ንፍቅና ጠራ። በእጁ ወይም በአንደበቱ ማውገዝ የቻለ ሰውና በነርሱ ላይ ይህንን ያወገዘ በርግጥ ከወንጀልና ከወንጀል ተባባሪነት ሰላም ሆኗል። ነገር ግን ድርጊታቸውን የወደደና በርሱ ላይ የተከተላቸው እነርሱ እንደጠፉት ይጠፋል።
ከዚያም ሶሐቦች ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ይህን አይነት ባህሪ የተላበሱ መሪዎችን አንዋጋምን?" ብለው ጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "በመካከላችሁ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስከሰገዱ ድረስ በፍፁም እንዳትዋጓቸው!" በማለት ከዚህ ከለከሏቸው።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ለወደፊት የሚከሰቱ ሩቅ ነገሮችን መናገራቸውና እንደተናገሩት መከሰቱ የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነቢይነት ከሚጠቁሙ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።
  2. ውግዝ ተግባርን መውደድና በርሱ ላይ መተባበር አይፈቀድም። ውግዝን ማውገዝም ግዴታ ነው።
  3. መሪዎች ከሸሪዓ የተፃረረን ነገር የፈጠሩ ጊዜ በዚህ ላይ እነርሱን መታዘዝ አይፈቀድም።
  4. በሙስሊም መሪዎች ላይ አምፆ መውጣት ያልተፈቀደው ይህን ተከትሎ ብክለት፣ ደም መፋሰስና የደህንነት ቀውስ ስለሚከሰት ነው። የወንጀለኛ መሪዎችን ውግዝ ተግባር መቻልና አስቸጋሪነታቸውን መታገስ ከነዚህ ነገሮች አንፃር እጅግ ቀላል ነው።
  5. ሶላት ጉዳዩዋ (ደረጃዋ) ትልቅ ነው። ሶላት በክህደትና ኢስላም መካከል የምትለይ መሆኗን እንረዳለን።

ትርጉሞችን አሳይ

58 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
JA 日本語 اليابانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
KMR Kurmancî الكرمنجية