عن أبي الدرداء رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ رَدَّ عَنْ عِرْضِ أَخِيهِ رَدَّ اللهُ عَنْ وَجْهِهِ النَّارَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ».
[صحيح] - [رواه الترمذي وأحمد]
المزيــد ...
ከአቡ ደርዳእ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።"
ሶሒሕ ነው። - ቲርሚዚ ዘግበውታል።
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙስሊም ወንድሙ በራቀ ወቅት እንዳይወገዝ ወይም በርሱ ላይ መጥፎ እንዳይደርስበት በመከልከል ከሙስሊም ወንድሙ ክብር ለተከላከለ ሰው አላህ የትንሳኤ ቀን ቅጣትን ከሱ እንደሚከላከልለት ተናገሩ።