عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«حَقُّ الْمُسْلِمِ عَلَى الْمُسْلِمِ خَمْسٌ: رَدُّ السَّلَامِ، وَعِيَادَةُ الْمَرِيضِ، وَاتِّبَاعُ الْجَنَائِزِ، وَإِجَابَةُ الدَّعْوَةِ، وَتَشْمِيتُ الْعَاطِسِ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

አቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡
"አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ላይ አምስት መብቶች አሉት፤ ሰላምታ መመለስ፣ ህመምተኛ መጠየቅ፣ ጀናዛን መሸኘት፣ ጥሪውን መቀበልና ባስነጠሰው ጊዜ 'የርሐሙከሏህ' ማለት ናቸው።'"

ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ወንድሙ ላይ ያለውን ጥቂት መብቶች ገለፁ። ከነዚህ መብቶች መካከል የመጀመሪያው ሰላምታ ለሰጠህ ሰላምታን መመለስ ነው።
ሁለተኛው መብት፡ ህመምተኛን መጠየቅና መዘየር ነው።
ሶስተኛው መብት፡ ጀናዛን ከቤቱ ወደ ሚሰገድበት ከዚያም ወደ መቃብሩ ተወስዶ እስኪቀበር ድረስ መሸኘት ነው።
አራተኛው መብት፡ ለሰርግም ይሁን ለሌላ ግብዣ ሲጠራ ጥሪውን አክብሮ ምላሽ መስጠት ነው።
አምስተኛ መብት፡ ሲያስነጥስ "ተሽሚት" ሊያደርግ ሲሆን ይሀውም አስነጥሶ "አልሐምዱሊላህ" (ትርጉሙም፡ ምስጋና ለአላህ ይገባው) ካለ "የርሐሙከሏህ" (ትርጉሙም፡ አሏህ ይዘንልህ) ይበለው፤ ከዚያም ያስነጠሰውም መልሶ "የህዲኩሙሏሁ ወዩስሊሕ ባለኩም" (ትርጉሙም፡ አሏህ ይምራህ ጉዳይህንም ያስተካክልልህ) ይላል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. እስልምና በሙስሊሞች መካከል ያሉ መብቶችን በማበርታትና በመካከላቸው ያለን ወንድማማችነትና መዋደድን በማጠናከር በኩል ያለውን ልቅና ያስረዳናል።