+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قال:
جَاءَ نَاسٌ مِنْ أَصْحَابِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَسَأَلُوهُ: إِنَّا نَجِدُ فِي أَنْفُسِنَا مَا يَتَعَاظَمُ أَحَدُنَا أَنْ يَتَكَلَّمَ بِهِ، قَالَ: «وَقَدْ وَجَدْتُمُوهُ؟» قَالُوا: نَعَمْ، قَالَ: «ذَاكَ صَرِيحُ الْإِيمَانِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 132]
المزيــد ...

አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦
የተወሰኑ የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባልደረቦች ወደነቢዩ በመምጣት እንዲህ ብለው ጠየቋቸው፦ " አንዳችን ለመናገር እጅግ የሚከብደንን ነገር ነፍሳችን ውስጥ እናገኘዋለን (በውስጣችን ይሰማናል)" እሳቸውም፦ "ይህን (በነፍሳችሁ ውስጥ) አገኛችሁን?" አሏቸው። እነሱም፦ "አዎን" አሉ። "ይህ ግልፅ ኢማን ነው።" በማለት መለሱላቸው።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 132]

ትንታኔ

የተወሰኑ የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባለደረቦች ወደርሳቸው በመምጣት አስቀያሚና እጅግ የሚፀየፉት በመሆኑ ሳቢያ ለመናገር የሚከብዳቸው የሆነ ነገር በነፍሳቸው ውስጥ ስለሚከሰት ትልቅ ጉዳይ ጠየቋቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "ይህ በውስጣችሁ የተሰማችሁ ነገር ግልፅ ኢማንና ሰይጣን በልባችሁ የሚጥለውን ለመከላከል የሚያነሳሳችሁ እንዲሁም በነፍሶቻችሁ ውስጥ እሱን መናገር እንድታወግዙና እንዲከብዳችሁ የሚያደርግ የእምነት እርግጠኝነት ነው። ሰይጣን ልቦችችሁን አልተቆጣጠረምና ነው። ሰይጣን ልቡን የተቆጣጠረው ግን ውስጡ የሚሰማውን እንዳይናገረው የሚከለክለውን አያገኝም።" በማለት መለሱላቸው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሰይጣን የኢማን ባለቤቶችን ከመወስወስ የዘለለ ምንም ነገር ማድረግ አለመቻሉ ደካማነቱን ይገልፅልናል።
  2. ነፍስን የሚያማልሉ ጉትጎታዎችን አለማመንና አለመቀበል እንደሚገባ። ምክንያቱም ከሰይጣን ነው።
  3. የሰይጣን ጉትጎታ አማኝን እንደማይጎዳ፤ ነገር ግን ከጉትጎታው በአላህ መጠበቅና በጉትጎታው ላይ ከማሰላሰል መቆጠብ እንደሚገባ።
  4. አንድ ሙስሊም በእምነቱ ጉዳይ ግራ ያጋባውን ዝም ማለት እንደማይገባና ስለርሱ መጠየቅ እንደሚገባው ተረድተናል።
ተጨማሪ