+ -

عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما قال:
سَمِعَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ رَجُلًا يَعِظُ أَخَاهُ فِي الْحَيَاءِ، فَقَالَ: «الْحَيَاءُ مِنَ الْإِيمَانِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 36]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ሰውዬ ወንድሙን በአይነአፋርነቱ ሲወቅሰው ሰሙና 'አይነአፋርነት ከኢማን ነው።' አሉት።

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 36]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድን ሰውዬ ለወንድሙ አይነአፋርነት ማብዛት እንዲተው ሲመክረው ሰሙትና አይነአፋርነት ከኢማን መሆኑን እና ከመልካም በስተቀር ይዞ እንደማይመጣ ገለፁለት።
አይነአፋርነት መልካም ድርጊት ለመስራትና እኩይ ተግባር ለመተው የሚያነሳሳ ስነምግባር ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከመልካም ተግባር የሚከለክል ባህሪ ተወዛጋቢነት፣ ደካማነት፣ ልፍስፍስነትና ፈሪነት እንጂ አይነአፋርነት አይባልም።
  2. ከአሏህ ሓያእ ማድረግ የሚሆነው ትእዛዛትን በመፈፀምና ክልከላትን በመተው ነው።
  3. ከፍጡራን ሐያእ ማድረግ የሚሆነው እነሱን በማክበር፣ በሚመጥናቸው ደረጃቸው ላይ በማስቀመጥና በተለምዶ ከሚያፀይፍ ድርጊት በመራቅ ነው።