+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«اجْتَنِبُوا السَّبْعَ الْمُوبِقَاتِ»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ وَمَا هُنَّ؟ قَالَ: «الشِّرْكُ بِاللهِ، وَالسِّحْرُ، وَقَتْلُ النَّفْسِ الَّتِي حَرَّمَ اللهُ إِلَّا بِالْحَقِّ، وَأَكْلُ الرِّبَا، وَأَكْلُ مَالِ الْيَتِيمِ، وَالتَّوَلِّي يَوْمَ الزَّحْفِ، وَقَذْفُ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ الْغَافِلَاتِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2766]
المزيــد ...

አቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡
"ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!" ሶሓቦችም: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ምን ምን ናቸው?" ብለው ጠየቁ፥ ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በአግባቡ ካልሆነ በስተቀር መግደል፣ አራጣ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ ጦርነት በተፋፋመ እለት ማፈግፈግ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ጥብቅ ምእመናትን በዝሙት መዝለፍ ናቸው።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2766]

ትንታኔ

የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኡመታቸውን ከሰባት አጥፊ ወንጀሎች እንዲርቁ አዘዙ። ምን ምን እንደሆኑ በተጠየቁ ጊዜም ተከታዮቹን ዘረዘሩ፡
የመጀመሪያው : በየትኛውም መልኩ ቢሆን ጥራት ለተገባው አላህ ቢጤን በማድረግ፤ ከአምልኮዎች መካከል ማንኛውም የአምልኮ ዘርፍን ከአሏህ ውጭ ላለ አካል በመስጠት አላህ ላይ ማጋራት መሆኑን ገለፁ፤ በሽርክ የጀመሩበት ምክንያትም ከወንጀሎች ሁሉ ትልቁ ወንጀል ስለሆነ ነው።
ሁለተኛ ድግምት፡ - እየቋጠሩ፣ እያነበነቡ፣ መድኃኒትና ጭሳጭስ እያደረጉ የሚሸርቡትን የሚጠቁም ገላጭ ቃል ሲሆን - ድግምቱ የተደረገበትን ሞት ወይም ህመም ላይ በመጣል፣ ወይም በባልና ሚስት መካከል መለያየትን በመፍጠር ተፅእኖ የሚያሳድር ነው። ድርጊቱ ሰይጣናዊ ስራም እንደመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ በሽርክ እና መጥፎ መናፍስት የሚወዱትን ነገር እያደረጉ ወደነርሱ በመቃረብ የሚከናወን ነው።
ሶስተኛ አስተዳደሩ ተግባራዊ በሚያደርገው ሸሪዓዊ ምክንያት ካልሆነ በቀር አሏህ እርም ያደረጋትን ነፍስ መግደል፤
አራተኛ በመብላትም ይሁን በሌላ መልኩ በመጠቃቀም ወለድን መውሰድ፤
አምስተኛ ለአቅመ አዳም ሳይደርስ አባቱ በሞተበት ታዳጊ ገንዘብ ላይ ወሰን ማለፍ፤
ስድስተኛ ከከሀዲያን ጋር ከሚደረገ ፍልሚያ ማፈግፈግ፤
ሰባተኛ ጥብቅ የሆኑ ጨዋ እንስቶችን መዝለፍ፤ እንደዚሁም ጨዋ ወንዶችን መዝለፍ፤

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht Azerisht الأوزبكية الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከባባድ ወንጀሎች በነዚህ ብቻ የተገደበ ሆኖ አይደለም፤ እነዚህ ለብቻ ሊጠቀሱ የቻሉት ከከባድነታቸውና ከአደገኝነትቸው አኳያ ነው።
  2. አንድ ሰው ነፍስን በመግደሉ ወይም ከእስልምና በኋላ በመካዱ ወይም ትዳር ቀመስ ከሆነ በኋላ ዝሙት በመፈፀሙ መግደል የተፈቀደ ሲሆን ይህም ተግባራዊ የሚደረገው በአስተዳደሩ ነው።