عن أبي مَرْثَدٍ الغَنَوِيّ رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«لَا تَجْلِسُوا عَلَى الْقُبُورِ، وَلَا تُصَلُّوا إِلَيْهَا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 972]
المزيــد ...
ከአቡ መርሠድ አልጘነዊይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 972]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መቃብሮች ላይ ከመቀመጥ ከለከሉ።
ልክ እንደዚሁ ቀብሩ ወደ ሰጋጁ ቂብላ አቅጣጫ በሆነ ጊዜ ወደ መቃብሮች ዞሮ ከመስገድም ከለከሉ። ይህም የተከለከለው ወደ ሺርክ ከሚያዳርሱ አንዱ ስለሆነ ነው።