عن أبي مسعود رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«إِذَا أَنْفَقَ الرَّجُلُ عَلَى أَهْلِهِ يَحْتَسِبُهَا فَهُوَ لَهُ صَدَقَةٌ».
[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...
ከአቡ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"ሰውዬው (ምንዳ እንደሚያገኝበት) እያሰበ ለቤተሰቡ ወጪ ያወጣ ጊዜ ለርሱ ምፅዋት ትሆንለታለች።"
ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሰውዬው እንደሚስቱ፣ ወላጆቹ፣ ልጁና ሌሎችንም እነርሱ ላይ ወጪ ማውጣት ግዴታ ለሆነበት አካል ሲሰጥ ወደ አላህ መቃረብንና አላህ ዘንድ ምንዳን እያሰበ ከሆነ ለርሱ የምፅዋት ምንዳ እንደሚሰጠው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።