عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ اللهَ إِذَا أَحَبَّ عَبْدًا دَعَا جِبْرِيلَ فَقَالَ: إِنِّي أُحِبُّ فُلَانًا فَأَحِبَّهُ، قَالَ: فَيُحِبُّهُ جِبْرِيلُ، ثُمَّ يُنَادِي فِي السَّمَاءِ فَيَقُولُ: إِنَّ اللهَ يُحِبُّ فُلَانًا فَأَحِبُّوهُ، فَيُحِبُّهُ أَهْلُ السَّمَاءِ، قَالَ ثُمَّ يُوضَعُ لَهُ الْقَبُولُ فِي الْأَرْضِ، وَإِذَا أَبْغَضَ عَبْدًا دَعَا جِبْرِيلَ فَيَقُولُ: إِنِّي أُبْغِضُ فُلَانًا فَأَبْغِضْهُ، قَالَ فَيُبْغِضُهُ جِبْرِيلُ، ثُمَّ يُنَادِي فِي أَهْلِ السَّمَاءِ إِنَّ اللهَ يُبْغِضُ فُلَانًا فَأَبْغِضُوهُ، قَالَ: فَيُبْغِضُونَهُ، ثُمَّ تُوضَعُ لَهُ الْبَغْضَاءُ فِي الْأَرْضِ».
[صحيح] - [صحيح مسلم] - [صحيح مسلم: 2637]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
«አላህ አንድን ባሪያ የወደደው ጊዜ ጂብሪልን ይጠራውና እንዲህ ይለዋል: "እኔ እከሌን እወደዋለሁና ውደደው።" ጂብሪልም ይወደዋል። ቀጥሎ ጂብሪል ሰማይ ውስጥ እንዲህ በማለት ይጣራል: "አላህ እከሌን ይወደዋልና ውደዱት።" የሰማይ ነዋሪዎችም ይወዱታል። ከዚያም ምድር ላይ ተቀባይነት ይኖረዋል። አላህ አንድን ባሪያ የጠላ ጊዜም ጂብሪልን በመጥራት እንዲህ ይለዋል: "እኔ እከሌን እጠላዋለሁና ጥላው።" ጂብሪልም ይጠላዋል። ቀጥሎም ጂብሪል ለሰማይ ነዋሪዎች እንዲህ በማለት ይጣራል: "አላህ እከሌን ይጠላዋልና ጥሉት።" እነርሱም ይጠሉታል። ከዚያም ምድር ላይ ተጠይነትን ይኖርበታል።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2637]
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ አንድን ትእዛዙን ታዛዥና ክልከላውን የሚርቅ አማኝ ባሪያውን የወደደ ጊዜ ጂብሪልን ይጣራል። አላህ እከሌን ይወደዋልና ውደደው። የመልአክቶች አለቃው ጂብሪል ዓለይሂ ሰላም ይወደዋል። ጂብሪልም ለሰማይ መልአክቶች ይጣራል። ጌታችሁ እከሌን ይወደዋልና ውደዱት። የሰማይ ነዋሪዎችም ይወዱታል። ቀጥሎ በአማኞች ቀልብ ውስጥ ለርሱ ውዴታን፣ ወደርሱ የመሳብንና በርሱ የመደሰትን ተቀባይነት እንዲኖረው ይደረጋል። አላህ አንድን ባሪያ የጠላ ጊዜም ጂብሪልን ይጣራል። እኔ እከሌን ጠልቼዋለሁና ጥላው። ጂብሪልም ይጠላዋል። ቀጥሎ ጂብሪል የሰማይን ነዋሪዎች ይጣራል። ጌታችሁ እከሌን ይጠላዋልና ጥሉት። እነርሱም ይጠሉታል። ከዚያም በአማኞች ቀልብ ውስጥ ለርሱ ጥላቻ እንዲኖር ይደረጋል።