+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنهما أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«أَتَدْرُونَ مَا الْمُفْلِسُ؟» قَالُوا: الْمُفْلِسُ فِينَا مَنْ لَا دِرْهَمَ لَهُ وَلَا مَتَاعَ، فَقَالَ: «إِنَّ الْمُفْلِسَ مِنْ أُمَّتِي يَأْتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ بِصَلَاةٍ وَصِيَامٍ وَزَكَاةٍ، وَيَأْتِي قَدْ شَتَمَ هَذَا، وَقَذَفَ هَذَا، وَأَكَلَ مَالَ هَذَا، وَسَفَكَ دَمَ هَذَا، وَضَرَبَ هَذَا، فَيُعْطَى هَذَا مِنْ حَسَنَاتِهِ، وَهَذَا مِنْ حَسَنَاتِهِ، فَإِنْ فَنِيَتْ حَسَنَاتُهُ قَبْلَ أَنْ يُقْضَى مَا عَلَيْهِ أُخِذَ مِنْ خَطَايَاهُمْ فَطُرِحَتْ عَلَيْهِ، ثُمَّ طُرِحَ فِي النَّارِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2581]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ድሃ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም: "እኛ ዘንድ ድሃ ማለት ዲርሀምና መጠቃቀሚያ እቃ የሌለው ሰው ነው።" አሉ። እርሳቸውም: "በኡመቴ ውስጥ ድሃ ማለት የትንሳኤ ቀን ሶላት፣ ፆም፣ ዘካ ይዞ የሚመጣ ነው። ነገር ግን ሲመጣ ይህንን ሰድቧል፣ ይህንን በዝሙት ዘልፏል፣ የዚህን ገንዘብ በልቷል፣ የዚህን ደም አፍስሷል፣ ይህንን መትቷል። ለዚህኛውም (ለተበዳዩ) ከመልካም ስራው ይሰጠዋል። ለዚያኛውም ከመልካም ስራው ይሰጠዋል። በርሱ ላይ ያለበት ሀቅ ተፈርዶ ሳይጠናቀቅ መልካም ስራው ካለቀ ደሞ ከነርሱ ወንጀል እየተወሰደ በርሱ ላይ ይጫንበትና ከዚያም እሳት ውስጥ ይጣላል።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2581]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባልደረቦቻቸውን: ድሀ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን? ብለው ጠየቁ። እነርሱም: በመካከላችን ድሃ የምንለው ገንዘብና እቃ የሌለውን ነው አሉ። እርሳቸውም: በኡመቴ ውስጥ የትንሳኤ ቀን ድሃ የሚባለው እንደ ሶላት፣ ዘካና ፆም የመሰሉ መልካም ስራዎችን ይዞ የሚመጣ ነው። (ነገር ግን) ሲመጣም ይህንን ሰድቦታል፣ ይህንን በክብሩ ዘልፎታል፣ የዚህን ገንዘብ በልቶ ክዶታል፣ የዚህን ደም አፍስሶ በድሎታል፣ ይህንን ደግሞ ደብድቦ አዋርዶታል። ለተበዳዮቹም ከምንዳዎቹ እየተቀነሰ ይሰጣቸዋል። እርሱ ላይ ያሉት ሐቆችና በደሎች ተፈርዶ ሳይጠናቀቅ መልካም ስራው ከተጠናቀቀ ከተበዳዩ ወንጀል ይወሰድና ወደ በዳዩ መዝገብ ይደረጋል። ከዚያም ምንም መልካም ስራ ስላልቀረው እሳት ውስጥ ተወርውሮ ይጣላል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية النيبالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ክልክል ተግባር ላይ ከመውደቅ መከልከሉ። በተለይም ቁሳዊና ሞራላዊ ከሆኑ የባሮች ሀቅ ጋር ተያያዥ ክልክሎች ላይ መውደቅ መከልከሉን እንረዳለን።
  2. የፍጡራን ሐቆች በመካከላቸው የሚፈታው በመካሰስ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ ከሺርክ ውጪ ያለ የፈጣሪ ሐቅ ግን የተመሰረተው በይቅርባይነቱ ላይ ነው።
  3. ሰሚን የሚያጓጓ፣ እይታውን የሚያዞር፣ ሀሳቡን የሚሰርቅ በሆነ መልኩ ውይይታዊ የማስተማር ስልትን መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን። በተለይ ጥቆማ በመስጠትና በማነፅ (ተርቢያ) ጉዳይ ላይ አስፈላጊ ነው።
  4. የትክክለኛ ድሃ ትርጓሜ መገለፁ። እርሱም: የትንሳኤ ቀን ሐቅ ያላቸው ሰዎች መልካም ስራዎቹን የወሰዱበት ሰው ነው።
  5. ቂሳስ (የሸሪዓዊ የማመሳሰል ቅጣት) በመጪው ዓለም ምንም ምንዳ እስከማይቀር ድረስ የሁሉም በጎ ስራዎችን ምንዳ እስከማጠናቀቅ ሊያደርስ እንደሚችል እንረዳለን።
  6. አላህ ከፍጡራን ጋር ያለው መስተጋብር በፍትህና እውነት ላይ የተመሰረተ ነው።