+ -

عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ قَرَأَ حَرْفًا مِنْ كِتَابِ اللهِ فَلَهُ بِهِ حَسَنَةٌ، وَالْحَسَنَةُ بِعَشْرِ أَمْثَالِهَا، لَا أَقُولُ {الم} حَرْفٌ، وَلَكِنْ {أَلِفٌ} حَرْفٌ، وَ{لَامٌ} حَرْفٌ، وَ{مِيمٌ} حَرْفٌ».

[حسن] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 2910]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።) (ይሄንን ስል) {አሊፍ ላም ሚም} አንድ ፊደል ነው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን {አሊፍ} አንድ ፊደል ነው። {ላም} አንድ ፊደል ነው። {ሚም} አንድ ፊደል ነው።'"

[ሐሰን ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2910]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ማንኛውም ከአላህ መጽሐፍ አንድ ፊደል የሚቀራ ሙስሊም ለርሱ ምንዳ እንዳለውና አንዱ ምንዳ ደግሞ ለርሱ በአምሳያው እስከ አስር ድረስ እንደሚባዛለት ተናገሩ።
ከዚያም ይህንን ({አሊፍ ላም ሚም} አንድ ፊደል ነው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን {አሊፍ} አንድ ፊደል ነው። {ላም} አንድ ፊደል ነው። {ሚም} አንድ ፊደል ነው።) በሚለው ንግግራቸው ሶስት ፊደል እንደሚሆኑና ሰላሳ ምንዳ እንደሚሆኑ ገለፁ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ቁርአን ማንበብ በማብዛት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. አንድ ቁርአን አንባቢ የሚያነባቸው ሁሉም ቃላት ውስጥ የሚገኙ ፊደላት በአስር አምሳያቸው የሚባዙ የሆኑ ምንዳዎች አሉት።
  3. አላህ ለባሮቹ በራሱ ቸርነት ምንዳዎችን ማባዛቱ የርሱ እዝነትና ቸርነት ሰፊ መሆኑን ያስረዳናል።
  4. ቁርአን ከሌሎች ንግግሮች በላይ ያለውን ብልጫና ማንበቡም አላህን ማምለኪያ መሆኑን እንረዳለን። ይህም እርሱ የአላህ ቃል ስለሆነ ነው።