عَنْ أَبِي عَبْدِ الرَّحْمَنِ السُّلَمي رحمه الله قَالَ:
حَدَّثَنَا مَنْ كَانَ يُقْرِئُنَا مِنْ أَصْحَابِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُمْ كَانُوا يَقْتَرِئُونَ مِنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَشْرَ آيَاتٍ، فَلَا يَأْخُذُونَ فِي الْعَشْرِ الْأُخْرَى حَتَّى يَعْلَمُوا مَا فِي هَذِهِ مِنَ الْعِلْمِ وَالْعَمَلِ، قَالُوا: فَعَلِمْنَا الْعِلْمَ وَالْعَمَلَ.
[حسن] - [رواه أحمد] - [مسند أحمد: 23482]
المزيــد ...
አቢ ዐብዲረሕማን አስሱለሚይ አላህ ይዘንላቸው እንዲህ አሉ፦
ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰሐቦች መካከል ቁርኣን ያስተምረን የነበረ አንድ ሰሐባ "ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አስር የቁርኣን አንቀፆችን ተምረው በተማሩት አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀትና ተግባር ሳይረዱ ሌላ ተጨማሪ አስር አንቀፆችን አይማሩም ነበር። በዚህም "ዕውቀትንም ተግባርንም ተማርን" አሉ።" ብሎ ነገረን።
[ሐሰን ነው።] - [አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሙስነድ አሕመድ - 23482]
ሰሐቦች -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አስር የቁርኣን አንቀፆችን ይቀስሙ ነበር። በቀሰሙት አስር አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀት እስኪረዱና እሱን ሳይተገብሩ ወደ ሌላ እውቀት አይሸጋገሩም ነበር።