عَنْ مُعَاذِ بْنِ جَبَلٍ رضي الله عنه:
أَنَّ رَسُولَ صَلَّى عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَخَذَ بِيَدِهِ، وَقَالَ: «يَا مُعَاذُ، وَاللَّهِ إِنِّي لَأُحِبُّكَ»، فَقَالَ: «أُوصِيكَ يَا مُعَاذُ لَا تَدَعَنَّ فِي دُبُرِ كُلِّ صَلَاةٍ تَقُولُ: اللَّهُمَّ أَعِنِّي عَلَى ذِكْرِكَ وَشُكْرِكَ وَحُسْنِ عِبَادَتِكَ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والنسائي وأحمد] - [سنن أبي داود: 1522]
المزيــد ...
ከሙዓዝ ቢን ጀበል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ :
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄን ያዙኝና እንዲህ አሉኝ: "ሙዓዝ ሆይ! ወላሂ እኔ እወድሃለሁ።" እንዲህም አሉ "ሙዓዝ ሆይ! ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።)
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን አቡዳውድ - 1522]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሙዓዝን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እጅ ያዙና ለርሱ እንዲህ አሉት: በአላህ እምልልሃለሁ እኔ እወድሃለሁ። ሙዓዝ ሆይ! በየሁሉም ሶላት መጨረሻ ላይ ይህን ማለት እንዳትተው አደራ እልሃለሁ። "አሏሁመ አዒኒ ዐላ ዚክሪከ" (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት አግዘኝ) ወደ አምልኮ የሚያቃርበኝ በሆነ ንግግርና ተግባር ሁሉ አግዘኝ። "ወሹክሪከ" ፀጋን በማግኘትና መከራን በማስወገድም (አንተን ለማመስገን) አግዘኝ። ለአላህ ስራን በማጥራትና ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመከተል (አምልኮህን በማሳመርም) አግዘኝ።