+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«أَقْرَبُ مَا يَكُونُ الْعَبْدُ مِنْ رَبِّهِ وَهُوَ سَاجِدٌ، فَأَكْثِرُوا الدُّعَاءَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 482]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 482]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ መሆኑን ገለፁ። ይህም ሰጋጅ ከሰውነቱ የላቀና የተከበረው አካሉን ለአላህ በሱጁድ ለመዋደቅ፣ ለመዋረድና ለመተናነስ ሲል መሬት ላይ የሚደፋ በመሆኑ ነው።
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሱጁድ ውስጥ ዱዓእ እንድናበዛም አዘዙን። በዚህም ንግግራዊም ድርጊታዊም መተናነስ ይሰባሰባሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አምልኮ ባሪያውን ወደ አላህ መቃረብን ትጨምርለታለች።
  2. ሱጁድ ዱዓእ ተቀባይነት ከሚያገኝበት ስፍራዎች መካከል አንዱ ስለሆነ ሱጁድ ውስጥ ዱዓእ ማብዛት እንደሚወደድ ተረድተናል።